በዘንድሮው የአልማ ሳምንት ሰፊ ሃብት ለማሠባሠብ ታቅዷል።

5

 

የአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) የማኅበሩን ዓላማ ለማሳካት እና የሕዝብ ንቅናቄ ለመፍጠር ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል በየዓመቱ የሚዘጋጀው የአልማ ሳምንት አንዱ ነው።

የዘንድሮውን የአልማ ሳምንት መርሐ ግብር በተመለከተ የአልማ ምክትል ዋና ሥራ አሥፈጻሚ አበረ ማኩሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም አልማ ማኅበረሰቡ የራሱን ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር በራሱ አቅም በብቃት እንዲፈታ የሚያስችል ርዕይ ቀርጾ እየሠራ ነው ብለዋል።

በትምህርት፣ በጤና፣ በሥራ ፈጠራ፣ በመልሶ መቋቋም እና በሌሎችም ዘርፎች ላይ ስትራቴጂክ ዕቅድ አዘጋጅቶ በሥፋት እየሠራ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

የዘንድሮው የአልማ ሳምንት ከሐምሌ1/2018 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 15/2018 ዓ.ም ድረስ ከማኅበሩ የ35ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ጋር በማቀናጀት እየተከበረ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

📌 በአልማ ሳምንት የሚከናወኑ ተግባራት:

👉 የ4 ነጥብ 6 ኪሎ ሜትር የአልማ ታላቁ ሩጫ በባሕር ዳር ይካሄዳል።

👉 በአልማ የተከናወኑ የማኅበረሰብ አቀፍ ፕሮጀክቶች ምረቃ እና ርክክብ ይፈጸማል።

👉የተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራዎች ይሠራሉ።

👉የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ይከናወናል።

👉የፎቶ ኤግዚቢሽን፣ የፓናል ውይይት እና የኪነ ጥበብ ዝግጅቶች ይካሄዳሉ።

👉 ልዩ ልዩ የሃብት ማሠባሠቢያ መርሐ ግብሮችም እንደሚካሄዱም አስታውቀዋል።

በዚህ ለሰባተኛ ጊዜ በሚከበረው የአልማ ሳምንት የሕዝብ ንቅናቄ በመፍጠር ሰፊ ሃብት ለማሠባሠብ መታቀዱንም ተናግረዋል።

📢 ኅብረተሰቡ በአልማ የልማት አጋርነት እያደረገ ስላለው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል። በአልማ ሳምንትም በንቃት እንዲሳተፍ እና ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

#አሚኮ #አልማ #የአልማ_ሳምንት #ኢትዮጵያ
#ባሕር_ዳር #ሐምሌ3_2018_ዓ_ም

ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleበምግብ ራስን መቻል ነጻነት እና ክብር ነው።
Next articleኢትዮጵያ ሽብርተኝነትን፣ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን እና ሌሎች የደኅንነት ስጋቶችን ለመከላከል በትኩረት እየሠራች ነው።