በሀረሪ ክልል ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሠበሠበ።

4

 

የሀረሪ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኀላፊ ያሲን አብዱላሂ የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚታቀዱ ፕሮጀክቶች ዕውን እንዲኾኑ በተለይም ገቢን በአግባቡ መሠብሠብ ወሳኝ ነው ብለዋል።

በተጠናቀቀው የበጀት ዓመትም የክልሉን ገቢ አሟጦ ከመሠብሠብ አንፃር ብዙ ርብርብ ሲደረግ መቆየቱን ገልጸዋል።

በዚህም በዓመቱ 4 ቢሊዮን 672 ሚሊዮን ብር ለመሠብሠብ ታቅዶ 4 ቢሊዮን 625 ሚሊዮን ብር በላይ በመሠብሠብ የዕቅዱን 99 በመቶ ማሳካት መቻሉን ገልጸዋል።

ከተሠበሠበው ገቢ መካከልም በቀጥታ ታክስ 2 ቢሊዮን 612 ሚሊዮን ብር በላይ፣ ቀጥታ ካልኾነ ታክስ 2 ቢሊዮን 211 ሚሊዮን ብር፣ ታክስ ነክ ካልኾነ ገቢ ደግሞ 275 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲሁም ከማዘጋጃ ቤት ገቢ ከ526 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሠብሠቡን ተናግረዋል።

የተሠበሠበው ገቢም አጠቃላይ ከታቀደው ዕቅድ አንፃር 99 በመቶ መኾኑን ጠቁመዋል። ገቢው ከ2017 በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀርም የ1ቢሊዮን 516 ሚሊዮን በላይ ብር ብልጫ እንዳለውም ጠቁመዋል።

በተለይም የውሰጥ መናበብን በማሳደግ፤ ቅንጅታዊ አሠራርን በማጎልበት፤ አገልግሎት አሰጣጥን በማሳደግ፤ በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሠራርን በመዘርጋት፤ ውዝፍ እዳን አሟጦ በመሠብሠብ፤ የቅሬታ አፈታት ሥርዓትን በማሻሻል፤ የታክስ ተደራሽነትን በማስፋት፤ ብቃት እና ተጠያቂነትን መሠረት ያደረገ የሰው ኀይል ስምሪት መተግበር መቻሉ ለገቢው ማደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳደረገ ተናግረዋል።

የአሠራር ሥርዓት ላይ የነበሩ መመሪያዎችን በማሻሻል ሕገ-ወጥ ነጋዴዎችን ወደ ሕጋዊነት የመቀየር ሥራ በትኩረት መሠራቱ የዓመቱ ዕቅድ እንዲሳካ አስችሏል ብለዋል።

በ2019 በጀት ዓመትም ከግብር ከፋዩ እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት የተሻለ ገቢ ለመሠብሠብ እና ለተጀመረው ክልላዊ እና ሀገራዊ የብልጽግና ጉዞ ኀላፊነትን ለመወጣት ዝግጅት እየተደረገ ስለመኾኑ አንስተዋል።

በዓመቱ የተሻለ ገቢ እንዲሠበሠብ አስተዋጽኦ ላደረጉ ግብር ከፋዮች፣ የተቋሙ ሠራተኞች፣ የክልሉ ከፍተኛ መሪዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ምሥጋና አቅርበዋል።

#አሚኮ_ዜና #ሀረሪ_ክልል #ገቢ #ኢትዮጵያ

#ባሕር_ዳር #ሐምሌ02_2018_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleሐምሌ አምስት ቀን ለሀገራዊ ለውጡ እርሾ የተጣለበት እና የሕወሃት ሽንፈት የተረጋገጠበት ቀን ነው።
Next articleየኢትዮጵያ ጤና ዘርፍ ስኬት 🇪🇹🏥