ለጥንቃቄ፦ ሰርጎ ገብ ጥቃት አሳሳቢ ኾኗል።

7
ባሕር ዳር: ሐምሌ 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ሰርጎ ገብ ጥቃት ማለት አንድ ያልተፈቀደለት አካል (Hacker) ወደ ግለሰቦች ወይም ተቋማት የኮምፒውተር መረብ፣ ሲስተም ወይም ዳታቤዝ ሰብሮ በመግባት መረጃዎችን ለመሰረቅ፣ ለማጥፋት ወይም ሲስተሙን ለመቆጣጠር የሚያደርገው ጥረት ነው።
መረጃዎች እንደሚያሳዩት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሰርጎ ገብ ጥቃቶች በከፍተኛ ኹኔታ እየጨመሩ ነው አኹን ላይ።
በኢመደአ መረጃ መሠረትም በ2018ዓ.ም በኢትዮጵያ ከተሞከሩ 50,155 የጥቃት ሙከራዎች ውስጥ
የሰርጎ ገብ ጥቃቶች ብዛት 20,601 ወይም 41በመቶ ነው።
👉ሰርጎ ገቦች የሚጠቀሟቸው ስልቶች፦
#የደህንነት ክፍተቶችን መፈለግ (Exploiting Vulnerabilities): በሲስተሞች ወይም ሶፍትዌሮች ላይ ያሉ ክፍተቶችን (Bugs) በመጠቀም መግባት።
#ማጭበርበር (Phishing): በኢ-ሜይል ወይም በቴክስት መልዕክት አሳሳች ሊንኮችን በመላክ የተጠቃሚ ስም እና የይለፍ ቃል በመስረቅ።
#ደካማ የይለፍ ቃላትን (Weak Passwords) በመስበር፦ በቀላሉ ሊገመቱ የሚችሉ የይለፍ ቃላትን በመሰበር መግባት
4. ተንኮል አዘል ሶፍትዌሮች (Malware): ቫይረሶችን ወደ ሲስተሙ በመርጨት የኋለኛ በር (Backdoor) በመክፈት።
💪እንዴት መከላከል ይቻላል?
#ጠንካራ የይለፍ ቃል መጠቀም፦ ፊደላት፣ ቁጥሮች እና ምልክቶችን ያካተተ ምስጢራዊ ቃል መጠቀም።
#ባለሁለት ደረጃ ማረጋገጫ (2FA)፦ ለፌስቡክ፣ ለኢሜይል እና ለሌሎች መተግበሪያዎች “Two-Factor Authentication” መተግበር።
#ሶፍትዌሮችን ማዘመን (Update)፦ ስልክ ወይም ኮምፒውተርን “Update” ሲጠይቅ ወዲያውኑ ማድረግ፤ ይህም አዳዲስ የደህንነት ክፍተቶችን ይደፍናል።
#የማይታወቁ ሊንኮችን አለመጫን፦ በኢሜይል ወይም በውስጥ መስመር የሚላኩ አጠራጣሪ ሊንኮችን ከመክፈት መቆጠብ
#የሳይበር ደህንነት ግንዛቤን ማሳደግ እንደሚገባ የኢመደአ መረጃ ያሳያል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ያገኘው ዓለም አቀፍ ዕውቅና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚወዳደሩ ባለሙያዎችን ለማፍራት የሚያስችል ነው።
Next article“ዛሬ በጎ ልብ በማሳየት ያገዝናቸው ታዳጊዎች በቀጣይ የማኅበረሰቡ አጋዥ ናቸው” ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ሙሉቀን ሰጥዬ