
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቴዎስ (ዶ.ር) በኢትዮጵያ የሳዑዲ ዓረቢያ አምባሳደር አብዱላህ ቢን ሀሰን አል-ዛህራኒን ዛሬ በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
በውይይቱ ወቅት ሚኒስትሩ በኢትዮጵያና በሳዑዲ ዓረቢያ መካከል ያለው የረጅም ዘመን የሁለትዮሽ ግንኙነትና ታሪካዊ ትስስር የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዋል።
ሁለቱ ወገኖች በጋራ ፍላጎቶች እና በወቅታዊ ቀጣናዊ ሰላምና ደኅንነት ጉዳዮች ላይ በስፋት የተወያዩ ሲሆን፤ በተለይም በተለያዩ የልማትና የኢኮኖሚ ዘርፎች ያለውን ሁለንተናዊ ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።
በተጨማሪም ውይይቱ በአሁኑ ወቅት በሳዑዲ ዓረቢያ በሚገኙ የኢትዮጵያ ዜጎች ወቅታዊ ሁኔታና መብት ጥበቃ ዙሪያ ላይ ያተኮረ እንደ ነበር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
