የኢትዮጵያ የግብርና ጉዞ ከተረጅነት ወደ ምግብ ሉዓላዊነት

5
🇪🇹
🌾🚀በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በግብርናው ዘርፍ ተጨባጭ ለውጥ ተመዝግቧል። ሀገሪቱ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የጀመረችው ጉዞ ተረጅነትን ታሪክ የሚያደርግ ጉዞ ነው።
በእስከ አሁኑ አፈጻጸም የላቀ ውጤት መመዝገቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ አስታውቀዋል።
🎯 በግብርናው ዘርፍ ዕድገት ለማምጣት በሀገር ደረጃ ምን እርምጃዎች ተወስደዋል?
👉 የፖሊሲ ማሻሻያ፦ መንግሥት ለግብርናው ዘርፍ ልዩ ትኩረት በመስጠት ዘርፉን የኢኮኖሚው ምሰሶ አድርጎ መቅረጹ ለግብርናው ዕድገት ትልቅ ሚና ተጫውቷል።
👉የግብርና ሜካናይዜሽን ማስፋፋት:- ግብርናው ከባሕላዊ አሠራር ወጥቶ በቴክኖሎጂ እንዲታገዝ፣ ትራክተሮች፣ ኮምባይነሮች እና የውኃ ፓምፖችን በስፋት ለአርሶ አደሮች እንዲደርሱ ተደርጓል።🚜🤖
👉የኩታ ገጠም አሠራርን መጠቀም:- በርካታ አርሶ አደሮች የግብርና ግብዓቶችን በውጤታማነት ለመጠቀም፣ የምርት ብክነትን ለመቀነስ፣ ጊዜን እና ጉልበትን መቆጠብ በመቻሉ ምርታማነትን አሳድጓል።
👉የግብዓት አቅርቦትን ማሻሻል :- በየዓመቱ በርካታ ቢሊዮን ዶላር ወጭ በማድረግ ምርጥ ዘር፣ የአፈር ማዳበሪያ እና ሌሎችንም ግብዓቶች ለአርሶአደሮች እንዲደርስ በቁርጠኝነት ሢሠራም ቆይቷል።
👉አገልግሎት ሰጭ ተቋማት እና የገበያ ትስስር ማስፋፋት:- አርሶ አደሮች የግብርና ግብዓቶችን በቅርበት የሚያገኙባቸው ማዕከላት በስፋት እንዲቋቋሙ ተደርጓል። የኢንዱስትሪ ፖርኮችን እና የአግሮ ፕሮሰሲንግ ማዕከላት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ተስፋፍተዋል።
🏭🍎
👉የተቀናጀ የመስኖ ልማት ሥራዎች🌊:-ወንዞችን፣ ጥልቅ ጉድጓዶችን እና አነስተኛ የውኃ አማራጮችን በመጠቀም በዓመት ሁለት እና ሦሥት ጊዜ ማምረት እንደሚቻል በተግባር ታይቷል።
✍️ በግብርናው ዘርፍ የመጡት ውጤቶች:-
✅ባለፉት አምሥት ዓመታት አጠቃላይ የግብርና ምርት ከ44 ሚሊዮን ቶን ወደ 150 ሚሊዮን ቶን አድጓል። በዚህም ከ3 እጥፍ በላይ የምርት ዕድገት አምጥቷል።
✅የዶሮ ስጋ ምርት ከ8 ሺህ ቶን ወደ 190 ሺህ ቶን ከፍ ብሏል። ይህም የ296 በመቶ ጭማሪ እንዳለ ያሳያል።
✅የደን ሽፋን ከ17 ነጥብ 2 በመቶ ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ አድጓል። ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኝ በመትከል 12 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት እንዲያገግምም ተደርጓል።🌲
✅ በ2018 በጀት ዓመት 29 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በማልማት 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ኩንታል ምርት ተሠብሥቧል።
✅ ቡናን ለውጭ ገበያ በማቅረብ በአንድ ዓመት ብቻ 3 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘት ተችሏል። ይህም የ17 ዓመታት የቡና ምርት ገቢን በአንድ ዓመት ማሳካት የተቻለበት ታሪካዊ ስኬት ኾኗል።☕💰
✅ቀደም ሲል ስንዴን ከውጭ በማስገባት በርካታ ዶላር ታወጣ የነበረውን ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ከሀገር ውስጥ ፍጆታ አልፎ ወደ ውጭ እየላከች የውጭ ምንዛሬ ማግኘት ጀምራለች።🌾
በድርቅ የሚታወቁት አካባቢዎች የምርት ማፈሻ ኾነዋል። እስካሁን ታርሰው የማያውቁ ሥፍራዎች በግብርና ልማት ተሸንፈዋል። ታይቶ የማይታወቅ ምርትም እየሰጡ ነው።
✅የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተጀመረው የሌማት ቱርፋት መርሐ ግብር አስገራሚ ውጤት ተገኝቶበታል።
✅የአቮካዶ፣ ሙዝ፣ ማንጎ፣ ፓፓያ እና ሌሎችንም የፍራፍሬ አይነቶች በስፋት በማምረት ለኢንዱስትሪዎች ግብዓት ኾኗል። ለአብነትም በአቮካዶ ምርት በአፍሪካ ሁለተኛዋ ለውጭ ገበያ የምታቀርብ ሀገር መኾን ችላለች።
የመጣው ለውጥ ለበለጠ ዕድገት የሚያነሳሳ እንጂ ኢትዮጵያ ካላት ሀብት እና በሚገባት ያክል እንዳልኾነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል። በቀጣይ ብዙ መሥራት እንደሚጠበቅም ጠቁመዋል።
📊ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ እያስመዘገበች ያለው ተጨባጭ ለውጥ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት የማረጋገጥ እና የተረጅነት ታሪክን የመቀየር ግስጋሴዋን እንድታስቀጥል አስችሏታል።
ዘጋቢ፦አሰፋ ልጥገበው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article“በ2019 በጀት ዓመት የላቀ እና ተጨባጭ ለውጥ የሚያመጡ አዳዲስ የትኩረት አቅጣጫዎች ተለይተዋል” ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ጋዜጠኛ ሙሉቀን ሰጥዬ
Next articleበሳዑዲ ዓረቢያ የኢትዮጵያ ዜጎች ወቅታዊ ሁኔታና መብት ጥበቃን በተመለከተ ውይይተ ተካሄደ።