በደቡብ ወሎ ዞን ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ትራክተሮች ለወረዳዎች እና ዩኒየኖች ተላለፉ።

10

 

በደቡብ ወሎ ዞን ከሞፈር ወደ ትራክተር እርሻ ለሚደረገው ሽግግር ከፍተኛ ሚና ያላቸው ትራክተሮች የክልል እና እና የዞን የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበት ለወረዳዎች እና ዩኒየኖች ተላልፈዋል።

የደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ ኀላፊ አሕመድ ጋሎ ዞኑ ለሜካናይዜሽን ምቹ መኾኑን ገልጸዋል። በሜካናዜሽን ሰፊ የሚታረስ መሬት እንዳለውም ጠቅሰዋል። አርሶ አደሮች የግብርና ሥራውን በቴክኖሎጂ በመታገዝ እንዲያከናውኑ ለማስቻል ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር እየተሠራ መኾኑንም አመላክተዋል።

ዛሬ ለወረዳዎች እና ለዩኒየኖች የተላለፉ የእርሻ ትራክተሮችም ምርት እና ምርታማነትን ለማሳደግ እገዛቸው የጎላ ይኾናል ነው ያሉት።

‎በርክክቡ የተገኙት በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አሥተባባሪ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር) የግብርና ሜካናይዜሽን አሠራርን በመከተል ምርት እና ምርታማነትን ለመጨመር እና ቴክኖሎጂን ለማስፋፋት እየተሠራ ነው ብለዋል።

ዛሬው ለወረዳዎች የተሰጡ ትራክተሮችም በዞኑ ያለውን የግብርና ሥራ ውጤታማ ለማድረግ እገዛቸው ከፍተኛ ነው ብለዋል።

‎ሜካናይዜሽንን በመጠቀም ምርት እና ምርታማነትን ለማሳደግ የቅንጅት ሥራ ማከናወን ላይ በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባም አሳስበዋል ።

#የግብርናሜካናይዜሽን #ደቡብወሎ #የግብርናቴክኖሎጂ #የምግብዋስትና #አሚኮ #SouthWello #AgriculturalMechanization

ዘጋቢ፦ ተመስገን አሰፋ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleዛሬ በጠረጴዛ ዙሪያ የምናሳየው መደማመጥ እና መቻቻል የነገዋ ኢትዮጵያ ውበት ነው።
Next articleባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ እና ቦይንግ ኩባንያ በትብብር ለመሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።