
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት አዲስ ከከፈተው የኤሮስፔስ ምህንድስና ጋር በተያያዘ በአቪየሽን ዘርፍ በትብብር መሥራት የሚያስችለውን ስምምነት ነው ከቦይንግ ኩባንያ ጋር የተፈራረመው።
የፊርማ ሥነ ሥርዓቱን የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት መንገሻ አየነ (ዶ.ር) እና የቦይንግ አፍሪካ ማኔጅንግ ዳይሬክተር አምባሳደር ሔኖክ ተፈራ አከናውነውታል።
ስምምነቱ ዩኒቨርሲቲው ለጀመረው የአቪየሽን ምህንድስና ትምህርት ብቁ የዘርፉ ባለሙያዎችን ለማፍራት፣ ለኢትዮጵያ የአቪየሽን ዘርፍ እድገት እና በአፍሪካ ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነቷን ለማስቀጠል ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ተገልጿል።
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢኖቬሽን እና የማኑፋክቸሪንግ ማዕከል የመኾን ዕቅዱን እውን ለማድረግም ትልቅ እርምጃ ነው ተብሏል።
#አሚኮ_ዜና #የባሕርዳር_ዩኒቨርሲቲ_እና_ቦይንግ_በጋራ_የመሥራት_ስምምነት #ኢትዮጵያ
#ባሕር_ዳር #ሐምሌ01_2018_ዓ_ም
ዘጋቢ፦ አድኖ ማርቆስ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
