ከሽፋን ወደ ጥራት፤ የኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፍ አዲስ ጉዞ !

4
🎓🇪🇹
ትምህርት የሀገር ብልጽግና መሰረት ነው። ይሁንና ባለፉት አስርት ዓመታት በኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፍ ስብራቶች ገጥመውት እንደቆዩ ይነገራል።
ባለፉት ዓመታት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እና ዘርፉን ከፖለቲካ እና ከብልሹ አሠራር ለማውጣት መጠነ ሰፊ የሪፎርም ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ። በተለይም እንደ ሀገር አዲስ የትምህርት ፍኖተ ካርተ ተቀርጾ እየተተገበረ ነው።
የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል ረገድም በርካታ ተግባራት ሢሠሩ ቆይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ በአነሳሽነት ወደ ሪፎርም የለውጥ ጉዞ እንዲገባ አድርገዋል። በዚህም ትምህርትን ከሽፋን ወደ ጥራት ለማሸጋገር የትምህርት ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ እየተደረገ ነው።
በዘርፉ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የትምህርት ሥርዓቱን መሠረት ከመቅረጽ ጀምሮ ጥራትን እስከማረጋገጥ የሚደረጉ ጥረቶች እጅግ አበረታች መኾናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ አስገንዝበዋል።
በዘርፉ የታዩ ቁልፍ ስኬቶች፦
👉ባለፉት ዓመታት ከ35 ሺህ በላይ የመዋዕለ ሕጻናት ትምህርት ቤት በመገንባት የትምህርት መሠረት ተጥሏል።
👉 በሺዎች የሚቆጠሩ ትምህርት ቤቶች ተገንብተዋል።
👉የኩረጃ ባሕልን በማስቀረት ተማሪዎች በራሳቸው ጥረት የሚመዘኑበት እና የቴክኖሎጂ አቅርቦት ተዘርግቶ ብቁ ትውልድ ለማፍራት ተግባራት ተከናውነዋል።
👉 እንደ ሀገር በችግር የተጎዱ ትምህርት ቤቶችን መልሶ በማደስ የትምህርት አገልግሎት ሳይስተጓጎል እንዲቀጥል ተደርጓል።
👉 በትምህርት አሰጣጥ ሂደቱ ላይ ቴክኖሎጂን በማቀናጀት ተማሪዎችን ብቁ እና የነገዋን ኢትዮጵያ ተረካቢ ለማድረግ እየተሠራ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
የዛሬ ታዳጊዎች ነገ ሀገር የሚገነቡ ናቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚህም ከመሠረቱ ልጆች ላይ በትኩረት እየተሠራ መኾኑን ለምክር ቤት አባላት ገልጸውላቸዋል።
ታዳጊ ልጆችን በዕውቀት እና በክህሎት ከመቅረጽ ባለፈ የሀገር ፍቅርን እና ትጋትን የተላበሱ ብቁ ዜጎችን ማነጽ ያስፈልጋል ነው ያሉት። ይህም “ትውልድ አድን እና ሀገርን የሚያሻግር ተግባር ነው ብለዋል።
​የመንግሥት የሪፎርም ሥራዎች በትምህርት ዘርፉ የነበሩ ሥብራቶችን በመጠገን ተስፋ ሰጪ ውጤቶች እያሳዩ እንደሚገኙም ገልጸዋል።
ነገ በዓለም አደባባይ ተርታ የምትሰለፍ ሀገር ለመገንባታ ዛሬ መሥራት ሀገራዊ ግዴታ እንደኾነም ተናግረዋል። ትምህርት የእድገት መነሻ ነውና፤ የተሻለች ኢትዮጵያን በጋራ መገንባት ያስፈልጋል ነው ያሉት 🇪🇹
በሥራውድንቅ ደሳለው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
#ምስል ከአርካይቭ
Previous article“ፍቱን መድኃኒቱ ምክክር ብቻ ነው”
Next articleየማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው እና የኢትዮጵያ አዲስ ምዕራፍ !