“ባለሀብቱን እና ኅብረተሰቡን በማሳተፍ የልማት ሥራዎችን ማፋጠን ይገባል” ሙሉነሽ ደሴ ( ዶ.ር)

5
‎የአማራ ክልል የማኅበራዊ ዘርፍ መሪዎች በጎንደር ከተማ የሚገኙ ማኅበራዊ ተቋማትን ጎብኝተዋል።
ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎቹ በጎንደር ከተማ የፋሲለደስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን፣ የጎንደር መምህራን ኮሌጅን፣ የአይራ ሆስፒታልን እና ሌሎች የጤና ተቋማትን ተመልክተዋል።
በፋሲለደስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በነበራቸው ምልከታም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎችን አበረታተዋል።
ጉብኝቱ በከተማዋ በማኅበራዊ ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን በተግባር በመመልከት የተሻሉ ተሞክሮዎችን ለማስፋት እና ችግሮችን ለመፍታት ያለመ መኾኑን በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አሥተባባሪ ሙሉነሽ ደሴ ( ዶ.ር) ተናግረዋል። በምልከታቸው በከተማዋ እየተሠሩ ያሉ መልካም ተግባራት መኖራቸውንም መታዘባቸውን አንስተዋል።
በቀጣይም ባለሀብቱን እና ኅብረተሰቡን በማሳተፍ የልማት ሥራዎችን ማፋጠን እንደሚገባ ነው መልዕክት ያስተላለፉት።
‎የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኀላፊ አብዱልከሪም መንግሥቱ በጎንደር ከተማ የሚገኙ የጤና ተቋማት ለሌሎች አካባቢዎች ተሞክሮ መኾን እንደሚችሉ አንስተው በሕክምና መሳሪያ እና መሠል ግብዓቶች ላይ ያሉ ጉድለቶችን ለመሙላት እንደሚሠራ ተናግረዋል።
‎ምልከታው ትምህርት ቤቶች እና የጤና ጣቢያዎች ያሉበትን ሁኔታ በመቃኘት ደረጃቸውን ለማሻሻል የሚያስችል መኾኑን የጠቀሱት የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ደብሬ የኋላ ናቸው። ምክትል ከንቲባዋ የኅብረተሰቡን አቅም በመጠቀም በሚፈለግበት ልክ ዘርፉን ለማሳደግ እንደሚሠራም ገልጸዋል።
‎ጉብኝቱ ከዚህ በፊት የተከናወኑ ሥራዎችን ውጤታማነት በመገምገም በቀጣይ ጊዜያት ለመደጋገፍ እና በቅንጅት ለመሥራት የሚያስችል መኾኑም ተመላክቷል።
ዘጋቢ፦ማርታ አዱኛ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article“የተጀመሩ የመንገድ መሠረተ ልማቶች እንዲጠናቀቁ በትኩረት ይሠራል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next article“ፍቱን መድኃኒቱ ምክክር ብቻ ነው”