“በአንድ ጊዜ ለብቻ ለማደግ የሚደረግ ጥረት ጎጂ ነው።” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

6

 

6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባ እንደቀጠለ ይገኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከምክር ቤት አባላት ገቢን በተመለከተ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።

ገቢ ላይ ሪፎርም በመካሄዱ እና ዲጂታላይዝድ በማድረግ 43 ሺህ ተቋማት መደበኛ ንግድ በማስገባት ገቢ መክፈል ጀምረውዋል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ባለፉት 27 ዓመታት የሰበሰበችው ገቢ 1 ትሪሊዮን እንደነበር አስታውሰው በ2018 በጀት ዓመት ብቻ ከ1 ነጥብ 5 ትሪሊዮን በላይ ገቢ ማግኘት እንደተቻለ ገልጸዋል።

ይህም 150 እጥፍ የሚበልጥ ነው ብለዋል። በቀጣይ ለነጋዴዎች ከሚታይ ገበያ ውጭ የሚደራደር ግብይት ካለ ይዘጋል ነው ያሉት። ባለ ሃብቶች ለማትረፍ እና ለመጠቀም ትክክለኛውን መንገድ ልትከተሉ ይገባል ብለዋል።

በአንድ ጊዜ ለብቻ ለማደግ የሚደረግ ጥረት ጎጅ እንጅ ጠቃሚ አይደለም ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ትልቅ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጋራ ጥረት ማሳደግ ይገባል ነው ያሉት። የኢትዮጵያ የ2018 በጀት ዓመት የወጭ ጉድለት 218 ቢሊዮን መኾኑንም ተናግረዋል።

ከማዕከላዊ ባንክ በመበደር ሳይኾን የግምጃ ቤት ሰነድ ግብይት እና ሌሎች ምንጮችን በመጠቀም የበጀት ጉድለትን ማሟላት ተችሏል ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስቴር ባለፉት ሁለት ዓመታት ከማዕከላዊ ባንክ ብድር ሳይበደር በጀት ዓመቱን ማጠናቀቁንም ጠቅሰዋል።

#ኢትዮጵያ #የሀገርውስጥገቢ #የሪፎርምውጤት #የበጀትዓመት #የምክርቤትስብሰባ #የኢኮኖሚዕድገት #ዲጂታላይዜሽን #አሚኮ
#ባሕርዳር_ሰኔ30_2018_ዓ_ም

በያየህ ፈንቴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleየደሞዝ ጭማሪ ተደረገ በሚል የሚዘዋወረው መረጃ ሀሰት ነው።
Next articleኢትዮጵያ ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት አስመዝግባለች።