የደሞዝ ጭማሪ ተደረገ በሚል የሚዘዋወረው መረጃ ሀሰት ነው።

2

 

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 30/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ ፊርማ ያለበት እና “የሠራተኞች የኑሮ ውድነት ጫና መደጎሚያ ደመወዝ ማሻሻያ ጥናት በገንዘብ ሚኒስቴር እና በሲቪል ስርቪስ ኮሚሽን በጋራ ተካሄዶ ለማክሮ አኮኖሚ ኮሚቴ ቀርቦ ታይቷል” የሚል መረጃ በማኅበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ ይገኛል።

የደመወዝ ጭማሪውም ከመስከረም 1/ 2019 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ለውሳኔ የቀረበ እንደኾነም ተጠቅሷል።

ነገር ግን መረጃው ሀሰት መኾኑን ተጻፈ በተባለበት ቀን ማረጋገጥ ይቻላል። ከስር የተያያዘው ደብዳቤ ላይ እንደሚታየው 28/12/2018 ዓ.ም ይላል ቀኑ። ይሄም የመረጃው ሀሰተኛነት ማረጋገጫ ነው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleኢትዮጵያ በአንድ ዓመት ብቻ 3 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ከቡና ወጪ ንግድ ገቢ አግኝታለች።
Next article“በአንድ ጊዜ ለብቻ ለማደግ የሚደረግ ጥረት ጎጂ ነው።” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)