ኢትዮጵያ በአንድ ዓመት ብቻ 3 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ከቡና ወጪ ንግድ ገቢ አግኝታለች።

2

 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ሥብሠባ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ነው።

በማብራሪያቸውም ኢትዮጵያ በተያዘው ዓመት ከቡና ወጪ ንግድ 3 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ በማግኘት በዘርፉ ታሪካዊ የተባለ ስኬት ማስመዝገቧን ገልጸዋል።

ሀገሪቱ ባለፉት 17 ዓመታት በድምሩ ከቡና ኤክስፖርት አግኝታ የነበረው ገቢ 3 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ብቻ እንደነበር አስታውሰዋል። ይሁን እንጂ ዘንድሮ በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ 3 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ በማግኘት ከሞላ ጎደል የ17 ዓመቱን ገቢ በአንድ ዓመት ማሳካት እንደቻለች ተናግረዋል።

በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ በቡና ምርት እና ወደ ውጭ በመላክ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሦስተኛ መኾን ችላለች ነው ያሉት። ይህ ታላቅ ሀገራዊ ውጤት በአጋጣሚ የመጣ ሳይኾን በዘርፉ ላይ በተደረገ የተቀናጀ ርብርብ ነው ብለዋል። ከዚህ ጎን ለጎንም ሀገሪቱ ተግባራዊ እያደረገችው ያለው የአረንጓዴ አሻራ የልማት መርሐ ግብር ለቡና ልማቱ የጎላ ጠቀሜታ ማበርከቱን አንስተዋል።

#ኢትዮጵያ #የኢትዮጵያቡና #የኤክስፖርትገቢ #የአረንጓዴአሻራ #የምክርቤትስብሰባ #የኢኮኖሚዕድገት #ታሪካዊስኬት
#ባሕርዳር_ሰኔ30_2018_ዓ_ም

በስማቸው አጥናፍ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article“የውጭ ግንኙነታችን የኢትዮጵያን የውሳኔ ሉዓላዊነት ማስጠበቅ መሠረት ያደረገ ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next articleየደሞዝ ጭማሪ ተደረገ በሚል የሚዘዋወረው መረጃ ሀሰት ነው።