“የውጭ ግንኙነታችን የኢትዮጵያን የውሳኔ ሉዓላዊነት ማስጠበቅ መሠረት ያደረገ ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

7

 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ሥብሠባ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ነው።

በማብራሪያቸውም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የዲጂታል እንቅስቃሴን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ 5 ሚሊዮን ወጣቶች የኮደርስ ሥልጠናን ወስደዋል ብለዋል።

ከ100 በላይ ቅርንጫፎች የሞሰብ ማዕከላት አገልግሎት እየሰጡ ነው፤ የሞባይል ባንኪንግ አጠቃቀም እያደገ ነው፤ የኤአይ (AI) ዩኒቨርስቲ ግንባታ እየተካሄደ ነው፤ ስታርት አፖች እየተስፋፉ እንደኾነም ገልጸዋል።

👉 የውጭ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን በተመለከተ ምን አነሱ?

ዓለም ተለዋዋጭ አሻሚ እና ኢ ተገማች በኾነ አውድ ውስጥ የሚንቀሳቀስ በመኾኑ ተቀያያሪ መሥፈርትን በመጠቀም መሥራት ያስፈልጋል ነው ያሉት።

የውጭ ግንኙነታችን የኢትዮጵያን የውሳኔ ሉዓላዊነትን ማስጠበቅን መሠረት አድርገን እየሠራን ነው ብለዋል።

✅ሦስት የ”መ”መርሆችን እንከተላለን ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

👉 መቋቋም:- ክፍተቶችን እያዩ መሙላት፤
👉መጠቀም:- ፈተናን ወደ ዕድል መቀየር፤
👉 መግራት:- የሰውን አጀንዳ መቀበል ሳይኾን የራስ አጀንዳ ፈጥሮ መግራትን መሠረት ተደርጎ እየተሠራ ነው ብለዋል።

በዓለም ዙሪያ ግጭት ሲፈጠር አፍሪካ ትራባለች የሚሉ ንግግሮች አሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ኢትዮጵያ አትራብም ሠርተን ራሳችንን እንመግባለን ብለዋል።

✅ የኢትዮጵያ ጠላቶች ሦስት የ”መ” ሥርዓቶችን ይከተላሉ:-

👉 መካድ፦ የነጻነት ሀገር መኾኗን፤ አልሸነፍ ባይነቷን ይክዳሉ ብለዋል። ኢትዮጵያን ማንበርከክ ቀላል አለመኾኑን ቢያውቁም ይክዳሉ ነው ያሉት።

👉 መርሳት:- ኢትዮጵያ የወጣቶች ሀገር መኾኗን፤ ወጣቱ ራሱን መከላከል እንደሚችል አያዩም ድህነታችንን እንጅ አልሸነፍ ባይነታችንን ይረሱታል ብለዋል።

👉ምኞት:- ያለፈ ስልት እስረኛ በመኾን የነበሩ ታሪኮችን በማንሳት መንግሥትን ለመጣል እንደሚመኙም አንስተዋል።

ሱዳን፣ ሻቢያ እና ወያኔ ቢጨመሩ በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ስጋት የለንም፤ መከላከል የሚያስችል አቅም እየገነባን እንገኛለን ነው ያሉት።

ኢትዮጵያ የሰላም በሯ ክፍት ነው፤ ቅድሚያ ሰላምን መሠረት አድርጋ እንደምትሠራም አብራርተዋል።

✅ ኢትዮጵያ ምን ትሁን ?

እንደ ግራር ዛፍ ሥሯ ጥልቅ መኾን፤ ከፍ ብሎ መብቀል፤ ራስን መከላከል የሚችል ቁመናን መፍጠር ያስፈልጋል ብለዋል።

ወንድሞቻችን እያስጠጋን በማገዝ ጠላቶቻችንን እየተከላከልን ውጤታማ ተግባራትን እየሠራን እንገኛለን ነው ያሉት። በውጭ በዲፕሎማሲ ግንኙነት ኢትዮጵያ ለቀጣይ 25 ዓመታት የምትመራበት ግልጽ ስትራቴጅ ማስቀመጧንም ገልጸዋል።

#አሚኮ_ዜናጨ#የሕዝብ_ተወካዮች_ምክር_ቤት_ስብሰባ #አማራ_ክልል_ኢትዮጵያ 🇪🇹
#ባሕርዳር_ሰኔ30_2018_ዓ_ም

በያየህ ፈንቴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article“45 በመቶ የሚኾነው የመድኃኒት አቅርቦት የሚመረተው በሀገር ውስጥ ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next articleኢትዮጵያ በአንድ ዓመት ብቻ 3 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ከቡና ወጪ ንግድ ገቢ አግኝታለች።