
6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ሥብሠባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት አካሂዷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከምክር አቤት አባላት ለተነሱት ጥያቄዎችም ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው እንደገለጹት ኢትዮጵያ በዓለም ተለዋዋጭ ተጽዕኖዎች እና የንግድ ሥርዓት ሳትናወጥ የተረጋጋ እና ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት አስመዝግባለች። ይህም ባለፉት ዓመታት የተደረገው የኢኮኖሚ ሪፎርም ውጤት መኾኑን አብራርተዋል።
✍️ በግብርናው ዘርፍ የመሥኖ ልማትን፣ የእርሻ መሬትን፣ በኩታገጠም ማምረትን፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና ምርጥ ዘርን በስፋት በመጠቀም አመርቂ ውጤት ተገኝቷል ነው ያሉት።
📌 ዘንድሮ 29 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በማልማት 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ኩንታል ምርት መሠብሠቡንም ተናግረዋል።
📌በሌማት ቱሩፋት መርሐ ግብር የተጀመረው ሥራም አስገራሚ ውጤት አግኝተንበታል ብለዋል።
📌በአቮካዶ ምርት በአፍሪካ ሁለተኛ ወደ ውጭ ላኪ ሀገር መኾን ችላለች ነው ያሉት።
📌በድምሩ በግብርናው ዘርፍ 7 ነጥብ 7 በመቶ እድገት ይመጣል ተብሎ እንደሚጠበቅም አስገንዝበዋል።
✍️ በኢንዱስትሪ ዘርፍም ትርጉም ያለው ዕድገት መምጣቱን ተናግረዋል።
📌ከለውጡ በፊት የነበሩት ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም ከ47 በመቶ በታች እንደነበርም ጠቁመዋል።
📌አሁን ላይ 67 በመቶ ማምረት መቻላቸውን ነው ያብራሩት። ከ10 በላይ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ተገንብተዋልም ብለዋል።
📌በቀጣዩ ዓመት ከኢንዱስትሪ ዘርፍ ከውጭ ገበያ 1 ቢሊዮን ዶላር እንደሚጠበቅም ጠቁመዋል።
📌 በዚህ ዓመት ከውጭ 5 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ተኪ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ማምረት እንደተቻለም አብራርተዋል።
📌በዚህ ዓመት ብቻ የአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ 20 ነጥብ 3 በመቶ ማደጉን ነው የተናገሩት።
📌የማዕድን ዘርፉ 24 በመቶ አድጓልም ብለዋል። በስሚንቶ ምርትም የ16 በመቶ ዕድገት መኖሩን አብራርተዋል።
📌በኀይል አጠቃቀም ደግሞ 23 በመቶ ዕድገት አለ ነው ያሉት።
📌በዚህ ዓመት አጠቃላይ የኢንዱስትሪው ዕድገት 12 ነጥብ 7 በመቶ እንደሚጠበቅም አብራርተዋል።
#አሚኮ_ዜና #የምክር_ቤት_ውሎ #PMAbiyAhmed #Parliament 🇪🇹
#ባሕር_ዳር_ሰኔ_30_2018_ዓ_ም
በአሰፋ ልጥገበው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
