የጎንጅ-ኮሬ-አዲሳለም የኮንክሪት አስፓልት መንገድ ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ኾነ።

2
በሰሜን ጎጃም ዞን ማኅበረሰቡ ለረጅም ጊዜ ሲጠብቀው የነበረው የጎንጅ–ኮሬ–አዲሳለም የ10 ነጥብ 74 ኪሎ ሜትር የኮንክሪት አስፓልት መንገድ ግንባታ ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት መኾኑ ተገልጿል።
መንገዱ ከአዲሳለም ከተማ በኩል ያለው እስከ 5 ኪሎ ሜትር የሚደርሰው የመንገድ ክፍል ባለ ሁለት አካፋይ ኾኖ እንዲገነባ
የተደረገ ነው።
ይህም ለከተማዋ ዘመናዊ ገጽታ እና ፈጣን ዕድገት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ተመላክቷል።
ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ መንገዶች አሥተዳደር አማካኝነት በኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የተገነባ ሲኾን የክልሉ መንግሥት ባደረገው ቀጣይነት ያለው ክትትል እና ድጋፍ በተሳካ ሁኔታ ሊጠናቀቅ ችሏል።
የክልሉ መንገድ ቢሮ እንዳስታወቀው ይህ ፕሮጀክት በአካባቢው ለረጅም ጊዜ ሲጠየቅ የነበረውን የመልካም አሥተዳደር ጥያቄ የመለሰ ሲኾን ለንግድ፣ ለትራንስፖርት፣ ለኢንቨስትመንት እና ለማኅበራዊ አገልግሎቶች መስፋፋት አዲስ ምዕራፍ ይከፍታል ተብሎም ተስፋ ተጥሎበታል።
#ባሕር_ዳር፡ ሰኔ 29/2018 ዓ.ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ነገ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ።
Next articleከታሪክ የማይማረው የሕወሓት የጥፋት ጉዞ