
#ባሕር_ዳር፡ ሰኔ 29፣ 2018
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ነገ ሰኔ 30/2018 ዓ.ም የመንግሥትን የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀርባሉ፡፡
6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባውን በነገው ዕለት ያካሂዳል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምክር ቤቱ ተገኝተው የመንግሥትን የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2019 ዓመታዊ በጀት ላይ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ የሚሰጡ ይሆናል፡፡
በስብሰባው ላይ ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዥ እንግዶች፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች ይሳተፋሉ፡፡
የምክር ቤቱ 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባ ነገ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ እንደሚካሄድ የምክር ቤቱ መረጃ አመልክቷል፡፡
