
የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልእክት፦
#ባሕር_ዳር ሰኔ 29/2018 ዓ.ም
ኢትዮጵያ በሕክምና ትምህርትና በዲጂታል ፈጠራ የአህጉራችንን የነገ ተስፋ ለመቅረጽ በቁርጠኝነት እየሠራች ትገኛለች!
የአህጉራችን ብሩህ ተስፋ ማሳያ በሆነችው ውቧ አዲስ አበባችን እየተካሄደ የሚገኘውን የአፍሪካ የሕክምና ትምህርት «MedEDAfrica 2026» አህጉራዊ ጉባኤን ዛሬ በይፋ ከፍተናል።
የአፍሪካ የነገ ጤና እና ተስፋ የሚወሰነው ዛሬ በምናዘጋጀው ወጣት የሕክምና ኃይል ላይ ነው፤ ኢትዮጵያ ደግሞ ለዚህ አህጉራዊ ግብ ቁርጠኝነቷን በተግባር እያሳየች ነው።
ባለፉት ጥቂት ዓመታት የጤና ባለሞያዎችን ትምህርት ለማስፋፋት ከፍተኛ ሙዓለ ንዋይ አፍስሰናል። በመላ ሀገሪቱ የሕክምና ትምህርትን ለማዳረስ ያልተማከለ ሥርዓት ዘርግተናል።
ሀገራችን ከራሷ አልፋ ከአፍሪካ ሀገራት የመጡ የጤና ባለሞያዎችን በከፍተኛ የሕክምና ትምህርት ተቋሞቿ በማስተማር እንደ ቀጣናዊ የልቀት ማዕከል እያገለገለች ትገኛለች።
በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ባለራዕይ መሪነት ሀገራችን በሰው ሠራሽ አስተውሎት እና በዲጂታል ፈጠራ የአህጉሪቱ መሪ ለመሆን ራሷን እያዘጋጀች ትገኛለች።
በአፍሪካ አህጉራችን ውስጥ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎቻችን፣ ሆስፒታሎቻችን እና የኢንዱስትሪው ዘርፍ በጋራ ሊሠሩ፣ የምርምር ውጤቶችም የፖሊሲ መመሪያ ሊሆኑና የሕዝቡን ሕይወት በተግባር ሊለውጡ ይገባል።
አብረን ካስተማርን፣ አብረን ፈጠራን ካመጣን፣ እና በጋራ ከመራን፣ እውቀት ሰብዓዊነትን የሚያገለግልባትን ጤናማ አፍሪካን እንገነባለን!
#አፍሪካ #ጤና_ጉባኤ #አሚኮ
