📱 የመሠረተ ልማት ሥርጭት ፍትሐዊነት እንዲረጋገጥ በትኩረት ተሠርቷል።

5

 

የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ የፓርላማ ዘመን 5ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው።

ምክር ቤቱ በጉባኤው ከገመገማቸው ሪፖርቶች መካከል የድጎማ በጀት እና የጋራ ገቢዎች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ይገኝበታል።

በቀረበው ሪፖርት እና በተሰጡ ማብራሪያዎች ዙሪያ ዋና ዋና የተባሉ ነጥቦች እንደሚከተለው ቀርበዋል፦

⚖️ የመሠረተ ልማት ፍትሐዊነትን በተመለከተ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር የመሠረተ ልማት ሥርጭት ፍትሐዊነት መጓደልን በተመለከተ ምክር ቤቱ በአግባቡ ክትትል ማድረጉን ገልጸዋል።

ባለፈው በጀት ዓመትም ኾነ ባለፉት 5 የምክር ቤቱ የጉባኤ ዘመናት “ምንም አይነት አዲስ የሥርጭት ኢ-ፍትሐዊነት የለም ብለዋል። ይህንንም በአግባቡ አረጋግጠናል” ነው ያሉት።

ይሁን እንጂ ይህ ማለት ታሪካዊ የቆዩ ኢ-ፍትሐዊነቶች የሉም ማለት አይደለም ያሉት አፈ ጉባኤው የቆዩ ክፍተቶችን ለማሟላት ሰፊ ሥራዎች እየተሠሩ መኾናቸውን ጠቁመዋል።

💰 የበጀት ዝውውር እና የጋራ ገቢዎች የቋሚ ኮሚቴው ፀሐፊ ኃይሉ ኢፋ ባቀረቡት ሪፖርት:-

ጥቅል በጀት፦ ከፌዴራል መንግሥት ወደ ክልሎች 304 ቢሊዮን ብር ተላልፏል። ይህም የዕቅዱን 96 ነጥብ 8 በመቶ ስኬታማ አድርጎታል።

የጋራ ገቢዎች እና ሮያሊቲ፦ ከፌዴራል ወደ ክልል እንዲሁም ከክልል ወደ ፌዴራል የተደረገው የጋራ ገቢዎች ዝውውር 259 ቢሊዮን ብር ደርሷል። በተጨማሪም 1ነጥብ 56 ቢሊዮን ብር የሮያሊቲ ክፍያ ተሰብስቧል።

🔄 የበጀት አሰጣጥ እና ቀመር የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ሽመልስ አብዲሳ በጥቅል በጀት ዙሪያ የሕግ ማሻሻያዎችን ከማድረግ ጀምሮ ፍትሐዊነታቸውን በ8 የፌዴራል መሥሪያ ቤቶች በኩል የማረጋገጥ ውጤታማ ሥራ መሠራቱን ገልጸዋል።

ውስን ዓላማ ያላቸው በጀቶች ግን አሁንም በቀጥታ በሥራቸው ለሚገኙ አሥፈጻሚ ተቋማት መተላለፋቸው እንደሚቀጥልም አብራርተዋል።

📊 የስታቲስቲክስ አገልግሎት አዲስ የሕዝብ ቆጠራ ሳያደርግ ምክር ቤቱ አዲስ ቀመር እንደማይሠራ በመወሰኑ በአሁኑ ወቅት የሕዝብ ቆጠራ ውጤት እየተጠበቀ መኾኑም ተመላክቷል።

ዘጋቢ:- አንዷለም መናን

#ኢትዮጵያ #አሚኮዜና #ምክርቤት
#Ethiopia #HouseOfFederation #EthiopianBudget #Infrastructure #FDRE
#አዲስ_አበባ_ሰኔ 29_2018ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleሕዝብ ራሱ አጀንዳ ቀርጿል፤ ራሱ መፍትሔም አመንጭቷል ! 🇪🇹
Next articleጤናማ አፍሪካን የመገንባት ጉዞ 🩺🌍