ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ 3ኛውን ሀገራዊ “የጽዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ ንቅናቄ” አስጀመሩ።

2

 

የአካባቢ ብክለት፤ የፕላስቲክ እና የኬሚካሎች አወጋገድ እንዲሁም የድምፅ ብክለት የአካባቢ ጉዳዮች ብቻ ሳይኾኑ የኢኮኖሚ ምርታማነት እና የሀገር የወደፊት እጣ ፈንታ ጋር በቀጥታ የተሳሰሩ ብሔራዊ የደኅንነት ጉዳዮች መኾናቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተናግረዋል።

ባለፉት ሁለት ዓመታት በተካሄደው ንቅናቄ ሚሊዮኖች በባለቤትነት የተሳተፉበት፤ የሕዝብ ግንዛቤ ያደገበት እና ሕግን በማስከበር ረገድ ትልቅ ውጤት የተመዘገበበት መኾኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውሰዋል።

ዛሬ የተጀመረው 3ኛው ንቅናቄ ስኬታማ የሚሆነው፦

➠ጅምር ሥራዎችን ይበልጥ በማስቀጠል፣

➠ክፍተቶችን በውጤት በመለካት እና

➠ቴክኖሎጂን በተግባር ላይ በማዋል እንደኾነ ነው የተናገሩት።

ኢትዮጵያ ባለፉት 7 ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ 48 ቢሊዮን ችግኞችን በመትከል እንዲሁም በኮሪደር ልማት ምቹ እና ውብ ከተሞችን በመፍጠር በአፍሪካ ተምሳሌታዊ ሥራዎችን መሥራቷን ያነሱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ሥራ በማስቀጠል ጽዳት እና ብክለትን መከላከል ሀገራዊ ባሕል ሊደረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ለ3ኛው “የጽዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ ንቅናቄ” ስኬታማነት የክልል እና የከተማ አሥተዳደር አመራሮች፣ ህዝቡ እና ባለድርሻ አካላት በልዩ ትኩረት እና በቅንጅት እንዲሰሩም ጥሪ አቅርበዋል።

#CleanEthiopia #GreenLegacy #Ethiopia #የፅዱኢትዮጵያ #አሚኮ
#አዲስ_አበባ #ሰኔ 27/2018

ዘጋቢ: ኢብራሂም መሃመድ

Previous articleየፍኖተ ሰላም መምህራን ኮሌጅ ተመራቂዎች አዲስ ምዕራፍ! 🎓 📜
Next article“የሰው ልጅን በዕኩል ዐይን የሚያገለግል ሆስፒታል ይገነባል” ርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ