የፍኖተ ሰላም መምህራን ኮሌጅ ተመራቂዎች አዲስ ምዕራፍ! 🎓 📜

12

 

#ፍኖተ_ሰላም: ሰኔ 27/2018 ዓ.ም
የፍኖተ ሰላም መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በመጀመሪያ ዲግሪ እና በዲፕሎማ በመደበኛ መርሐግብር ያሠለጠናቸውን እጩ መምህራን አስመርቋል ።

ኮሌጁ ለመጀመሪያ ጊዜ በመጀመሪያ ዲግሪ 236 ተማሪዎችን፤ በዲፕሎማ መርሐ ግብር ደግሞ ለ14ኛ ዙር 217 እጩ መምህራንን ነው ያስመረቀው።

የኮሌጁ ተወካይ ዲን ዘውዱ ፈንቴ ባለፉት በነበሩት የጸጥታ ችግሮች ሳትበገሩ ከችግር በላይ ኾናችሁ ለዚህ በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

ተመራቂዎች ከመደበኛው የመማር ማስተማር ሥራው በተጨማሪም የኮደርስ ሥልጠናንም ጭምር ወስደው ያጠናቀቁ መኾናቸውን ገልጸዋል።

የፍኖተ ሰላም ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ጊዜው ደግአረገ ከተማ አሥተዳደሩ ለትምህርት ዘርፍ ትኩረት በመስጠት የትምህርት መሠረተ ልማቶችን እያስፋፋ መኾኑን አንስተዋል።

የትምህርት ተቋማት ትውልድን በመገንባት መሠረት መኾናቸውንም ገልጸዋል። ተቋማቱ የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ሰላምን መጠበቅ ወሳኝ ነውም ብለዋል።

የዛሬው ምርቃት የመጨረሻ ሳይኾን ለቀጣይ ሕይወት መሸጋገሪያ ቁልፍ እንደኾነ ነው የተናገሩት።

አስተያየታቸውን የሰጡ ተመራቂ እጩ መምህራን ያሉ ችግሮችን በመቋቋም ለምረቃ በመብቃታቸው ልዩ ስሜት እንደሰጣቸው ተናግረዋል። በተለይ ሙያዊ መርሕን አጥብቆ በመያዝ እና በትምህርት ጥራት የሚስተዋሉ ችግሮችን በማከም ትውልድ ግንባታ ላይ የበኩላቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።

#ፍኖተ_ሰላም #መምህራን_ኮሌጅ #FinoteSelam #TeachersCollege #Graduation2026

ዘጋቢ ፦ ንጉስ ስንታየሁ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleየሕጻናት እና የሴቶች ደኅንነት መጠበቅ የሁሉም ኀላፊነት ሊኾን ይገባል።
Next articleምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ 3ኛውን ሀገራዊ “የጽዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ ንቅናቄ” አስጀመሩ።