“ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ጥበቃ ስኬታማ ሥራዎችን ሠርታለች” ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ.ር)

4
ባሕር ዳር: ሰኔ 16/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአውሮፓውያኑ ታዋቂ የፖሊሲ አጥኚ ተቋም ቻተም ሃውስ በለንደን ባዘጋጀው የአየር ንብረት ሳምንት የውይይት መድረክ ላይ የኢትዮጵያ ልዑክ ተሳትፏል።
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የኮፕ 32 ተሰያሚ ፕሬዝዳንት ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ.ር) “በተከፋፈለ ጂኦ-ፖለቲካዊ ሁኔታ ውስጥ የኮፕ ጉባኤዎችን አስፈላጊነት ማጉላት” በሚል መሪ መልዕክት በተካሄደው በዚህ መድረክ የኢትዮጵያን አቋም አብራርተዋል።
በከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ መድረኩ ላይ የኮፕ 30 ፕሬዝዳንት አንድሬ ኮሬያ ከብራዚል፣ የኮፕ 31ን የወከሉት የቱርክ የአካባቢ፣ የከተማ ልማት እና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስትር፣ ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የኮፕ 32 ተሰያሚ ፕሬዝዳንት ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ.ር) ጋር በጋራ በውይይቱ ላይ ተሳትፈዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ.ር) ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ጥበቃ ረገድ ያላትን ጠንካራ ርዕይ እና አመርቂ አፈጻጸም አንስተዋል።
በተለይም ባለፉት ስምንት ዓመታት ውስጥ በጠንካራ ፖሊሲ ተደግፈው ተግባራዊ የተደረጉ ሀገራዊ ስኬቶችን አጽንኦት ሰጥተው ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ኢትዮጵያ በምታዘጋጀው የኮፕ 32 ጉባኤ ላይ ቀዳሚ ተግባሯ የሚኾነው በቱርክ እና አውስትራሊያ በጋራ በሚዘጋጀው የኮፕ 31 የሚገኙ ስኬታማ ውጤቶችን መሠረት በማድረግ ቀጣይነትን ማረጋገጥ እንደኾነ ጠቁመዋል።
ይህ ዓይነቱ ስትራቴጂካዊ አካሄድም ከቀደሙት አዘጋጅ ሀገራት ጋር በቅንጅት በመሥራት የጋራ ተግባራትን ማጠናከር እና በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲያዊ ሂደት ላይ ያለውን ዓለም አቀፋዊ ተስፋ መልሶ ማቀጣጠል የሚለውን የኢትዮጵያን “መደመር” መርህ በግልጽ የሚያንጸባርቅ መኾኑን ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleበማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ሲንቀሳቀስ የነበረውን ጽንፈኛ ቡድን መደምሰሱን የሀገር መከላከያ ሠራዊት አስታወቀ።
Next article“ሀኪም ጋራ ኢኒሼቲቭን በመደመር መንግሥት ዕይታ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው” ርእሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ