በክረምት መግቢያ ወቅት የሚጠበቁ የጤና ስጋቶች የትኞቹ ናቸው?

2

 

ባሕር ዳር: ሰኔ 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የክረምት መግቢያ ወቅትን ተከትሎ የተለያዩ የጤና ስጋቶች ሊከሰቱ ይችላሉ። የአማራ ክልል የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትም በክልሉ በዚህ ወቅት ስጋት ሊኾኑ የሚችሉ የጤና ችግሮችን ለይቻለሁ ማለቱ ይታወሳል።

✍️ስጋት የተባሉት የትኞቹ ናቸው?

በኢንስቲትዩቱ መረጃ መሠረት ወባ እና ኮሌራ ዋነኛ ስጋቶች ናቸው። ​ኩፍኝ፣ ውሻን የሚያሳብድ በሽታ እና እከክም በዚህ ወቅት ተጨማሪ ስጋት ናቸው።

ኢንስቲትዩቱ ሥጋቶችን የለየው ያለፉ ዓመታትን የበሽታዎችን ሥርጭት መረጃዎች መሠረት በማድረግ እና የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ባስቀመጠው መለኪያ መሠረት መኾኑን የኢንስቲትዩቱ የኅብረተሰብ ጤና አደጋዎች ዝግጁነት አሥተባባሪ አበበ ሲሳይ ለአሚኮ መግለጻቸው አይረሳም።

✍️ስጋቱን ለመቀነስ ምን ተሠራ?

​የኅብረተሰብ ጤና አደጋዎች ዝግጁነት አሥተባባሪው አበበ ሲሳይ ኢንስቲትዩቱ በ36 በሽታዎች ላይ ቀጣይነት ያለው ክትትል እያደረገ ይገኛል ብለዋል።

እንደሥተባባሪው ገለጻ የበሽታዎችን ሥርጭት በቅርበት ለመከታተልም ጠንካራ የቅኝት (Surveillance) ሥርዓት ተዘርግቷል።

ማንኛውም የጤና አደጋ ቢከሰት ፈጣን እርምጃ መውሰድ የሚያስችል “የአደጋ ጊዜ ምላሽ ቅድመ ዝግጅት ዕቅድ” ተዘጋጅቶ ወደ ሥራ ተገብቷል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኢትዮጵያ 🇪🇹 አዲስ የዲፕሎማሲ ምዕራፍ ከቀጣናዊ ተፅዕኖ እስከ ዓለም አቀፍ ትኩረት
Next articleየኢትዮጵያን ተደማጭነት ከፍ ያደረገው የአረንጓዴ አሻራ ዲፕሎማሲ