በአማራ ክልል ለ2018 ዓ.ም

2
🌴አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ከ261 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት ተዘጋጅቷል።
ባሕር ዳር: ሰኔ 09/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ እና የተፋሰስ ልማትን በተመለከተ ለምዕራብ አማራ ለዞን እና ለወረዳ የተፈጥሮ ሀብት ልማት እና ጥበቃ ቡድን መሪ እና ባለሙያዎች ሥልጠና እየሰጠ ነው።
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኀላፊ መሰሉ ብርሃኑ ሥልጠናው በ2018 በጀት ዓመት የተሠሩ የተፈጥሮ ሀብት ልማቶችን በመገምገም የቀጣይ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር አፈጻጸምን ለማሻሻል ያለመ መኾኑን ተናግረዋል።
✅ በ2018 ዓ.ም በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ምን ተሠራ?
👉ከ9ሺህ 200 በላይ ተፋሰሶች ከ499 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት የማልማት ሥራ ተከናውኗል።
👉 4 ነጥብ 3 ሚሊዮን አርሶ አደሮች በሥራው ላይ ተሳትፈዋል።
የተፋሰስ ልማትን አርሶ አደሮች በባለቤትነት እየጠበቁ እና እየተንከባከቡ ይገኛሉም። አርሶ አደሮች🍋 በፍራፍሬ ልማት ተጠቃሚ መኾናቸውንም ተናግረዋል።
🌳በክልሉ በ2018 በጀት ዓመት የሚተከል ምን ያክል ችግኝ ተዘጋጅቷል?
👉በክልሉ ከ1 ነጥብ 76 ቢሊዮን በላይ ችግኝ ተዘጋጅቷል።
👉ማኅበረሰቡን በማሳተፍ ውጤታማ ችግኝ ተከላን ለማከናወን እየተሠራ ነው።
👉ከ261 ሺህ በላይ ሄክታር መሬትም ተዘጋጅቷል።
👉የችግኝ ተከላ ሥራው በዲጅታል ክትትል የሚደረግበት ነው።
በ2017 ከተተከሉ ችግኞች ውስጥ 80 ነጥብ 1 በመቶ መጽደቁንም ምክትል ቢሮ ኀላፊዋ ተናግረዋል።
በክልሉ በሰባት ዓመት ውስጥ 10 ነጥብ 4 ቢሊዮን ችግኝ መተከሉን ገልጸዋል። በዚህም 14 ነጥብ 6 በመቶ የነበረውን የደን ሽፋን ወደ 18 ነጥብ 9 በመቶ ማድረስ ተችሏል ብለዋል።
ይህም አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ አድርጓል ነው ያሉት። አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የደን እና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ያላቸው ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት መደረጉንም አንስተዋል።
የውይይቱ ተሳታፊ የዘርፉ ባለሙያዎች ከአርሶ አደሮች ጋር በቅንጅት መሥራታቸውን ተናግረዋል። የችግኝ መትከያ ጉድጓዶች ቀድመው ማዘጋጀታቸውንም አንስተዋል።
ሥልጠናው አቅምን የሚያሳድግ እና ውጤታማነትን ከፍ የሚያደርግ ነው ብለዋል።
ዘጋቢ:-ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleበምዕራብ ጎጃም ዞን 418 ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለዋል።
Next articleበአዲስ አበባ 24 ፈጣን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ኃይል መሙያዎች ዛሬ ሥራ ጀምረዋል፡፡