
ባሕር ዳር: ሰኔ 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የምርጫ ደኅንነት አፈጻጸም ግምገማ እና የቀጣይ ዕቅዶች ላይ ተወያይቷል።
የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ጄኔራል ዘላለም መንግሥቴ (ዶ.ር) የጸጥታ ኃይሉ ሀገር ለማቆም እና ሀገር ለማስቀጠል ከፍተኛ ዋጋ መክፈሉን ገልጸዋል።
ከውስጥ እና ከውጭ ያሉ ኃይሎች ክልሉን ለማፍረስ መረባረባቸውን ጠቁመዋል። ይህ ግን በጸጥታ ኃይሉ ከፍተኛ ርብርብ መክሸፉን እና ምርጫውን በስኬት ማጠናቀቅ መቻሉን አስታውቀዋል።
ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ ላደረጉ የክልሉ የጸጥታ ኃይል፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል የጸጥታ እና የደኅንነት አካላትን አመስግነዋል። “የቀጣይ ትኩረታችን ሰላምን በዘላቂነት ማስፈን ነው” ብለዋል።
በቀጣይም የክልሉን የሰላም ሁኔታ ለማሻሽል በሚሠራው ተግባር የጸጥታ ኃይሉ በትኩረት እንዲሠራ አሳስበዋል።
የፖሊስ መሪዎች እና አባላትም ምርጫው የጸጥታ ኃይሉ ከፍተኛ ሙያዊ ወኔ የታየበት፣ ሕዝቡ ከፖሊስ ጎን መቆሙ በተግባር የተረጋገጠበት መኾኑን ተናግረዋል።
ምርጫውን በስኬት ለማጠናቀቅ የተሠራውን ሥራ የሕግ የበላይነትን ለማስፈን በሚደረገው ጥረት በመድገም ሕዝብን ከጸጥታ ስጋት ማውጣት ይገባል ብለዋል።
ዘጋቢ፦ ስማቸው አጥናፍ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
