በመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ እና አሥተዳደር ለውጥ የሕዝብን እርካታ ለማረጋገጥ እየተሠራ ነው።

21

 

ባሕር ዳር: ሰኔ 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ በመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ እና አሥተዳደር ሪፎርም ዙሪያ ከሚዲያ እና የሕዝብ ግንኙነት መሪዎች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።

​የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኅላፊ ባንቺአምላክ ገብረማሪያም የመድረኩ ዋና ዓላማ የሪፎርሙን አፈጻጸም፣ የዝግጅት ምዕራፍ ሁኔታ እና በቀጣይ የሚወሰዱ አቅጣጫዎችን ለማስገንዘብ መኾኑን ገልጸዋል። በመንግሥት ተቋማት የሚከናወነው ይህ የለውጥ ሥራ ተደራሽ፣ ቀልጣፋ እና ግልጽ የኾነ አገልግሎት ለሕዝብ ለመስጠት ትልቅ ድርሻ እንዳለው አስገንዝበዋል።

​ሪፎርሙ በሦሥት ዋና ዋና ምዕራፎች በዝግጅት፣ በአፈጻጸም እና በማጽናት የተከፋፈለ ነው። በአሁኑ ወቅት በስምንት ተቋማት የዝግጅት ምዕራፉ በስኬት እየተከናወነ እንደሚገኝ ነው የተናገሩት።

​በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም የ”መሶብ አንድ ማዕከል” አገልግሎትን የማስፋፋት ሥራ እየተሠራ መኾኑን የገለጹት ኅላፊዋ ይህ ሥራ ተጠያቂነትን፣ ግልጽነትን እና የሕዝብ እርካታን ለማረጋገጥ ወሳኝ መኾኑን አንስተዋል።

በተለይ የመንግሥት ሠራተኞችን ብቁ፣ ውጤታማ እና ተወዳዳሪ ለማድረግ ዲጂታል የመረጃ ሥርዓት የመገንባት ሥራ ይሠራል ብለዋል።

​ሪፎርሙ ከቀበሌ እስከ ክልል ባሉ መዋቅሮች አገልግሎቱን አካታች እና ቀልጣፋ በማድረግ የዜጎችን እርካታ ማረጋገጥ ነውም ብለዋል። ለዚህም ብቁ፣ ነጻ እና ገለልተኛ ሙያተኛ መገንባት እንደሚያስፈልግም አጽንኦት ሰጥተዋል።

የሚዲያ እና የሕዝብ ግንኙነት አካላት ይህንን የመንግሥት የለውጥ ሥራ ለኅብረተሰቡ እና ለመንግሥት ሠራተኞች በማስተዋወቅ፣ በዝርዝር በማስረዳት በኩል ትልቅ ኀላፊነት እንደሚጠበቅባቸውም አስገንዝበዋል ።

#አሚኮ_ዜና #የመንግሥት _ሠራተኞች_የሪፎርም_ሥራ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ

ዘጋቢ፦ ሥራውድንቅ ደሳለው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የባዕዳን እና የባንዳዎችን አፍራሽ ተልዕኮ ማምከን የሠራዊታችን የቆየ ልምድ እና ተግባር ነው” ሌትናል ጄኔራል መሐመድ ተሰማ
Next articleበሕግ እንደሚያስጠይቅ ያውቃሉ?