“በመስዋዕትነት የጸና፣ በፈተና ያለፈ፣ ፈተናን የሚሻገር የጸጥታ ኀይል እየገነባን ነው”

13

 

ባሕር ዳር: ሰኔ 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ እና ስኬታማ ኾኖ ተጠናቅቋል። ለምርጫው ስኬታማነት ደግሞ የክልሉ የጸጥታ ኀይል ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጋር በቅንጅት በመሥራት ስኬትን አስመዝግበዋል።

የአማራ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ እሸቱ ዬሱፍ (ዶ.ር) ከአሚኮ ዲጅታል ክፍል ጋር በነበራቸው ቆይታ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ 🗳️ የታየውን የጸጥታ ስኬት ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል እየተሠራ ነው ብለዋል።

የምርጫ ጣቢያዎችን እና ቁሳቁስ ደኅንነት በመጠበቅ፣ የጥፋት ኀይሉ የምርጫ ሂደቱን እንዳያደናቅፍ ሰላምን በማስከበር የጸጥታ ኀይሉ ውጤታማ ተግባርን አከናውኗል ነው ያሉት።

ማኅበረሰቡ ከጸጥታ ኀይሉ ጎን በመኾን፣ ሰላሙን በማጽናት በድምጹ ይመራኛል ያለውን መንግሥት መርጧል ብለዋል።

🗳️ከስኬታማው የምርጫ ሂደት ሕዝብ የደገፈው ማንኛውም ተግባር ውጤታማ እንደሚኾን ትምህርት የተገኘበት መኾኑን ተናግረዋል።

“እያንዳንዱ ፈተና ለድል አብቅቶናል” ያሉት ቢሮ ኀላፊው የጸጥታ ኀይሉ ጽናትን እንደተማረበት ገልጸዋል።

በመስዋዕትነት የጸና፣ በፈተና ያለፈ፣ ፈተናን የሚሻገር፣ ነገን መምራት የሚችል የጸጥታ ኀይል እየገነባን ነውም ብለዋል።

በቀጣይ የጸጥታ ኀይሉን ይበልጥ ሥልጠና በመስጠት፣ ማኅበረሰቡ ጋር በቅንጅት በመሥራት፣ የሰላም እሴት ግንባታ ላይ ትኩረት በማድረግ እና በሌሎች ተግባራት ውጤታማ የጸጥታ ተግባርን ለመፈጸም እንደሚሠራም አመላክተዋል።

#አሚኮ_ዜና #ሰላምና_ጸጥታ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ 🇪🇹

ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleኮሚሽኑ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿ ተስፋ የጣሉበትን ታሪካዊ የምክክር ኀላፊነት ለመወጣት ዝግጁ ነው።
Next articleልማትን ከኅብረተሰብ ተጠቃሚነት ጋር አስተሳስሮ በመሥራት ወልድያ ተሞክሮ ኾናለች።