ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ለሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ።

1

 

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ለሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው ናሬንድራ ሞዲ በሕንድ ታሪክ ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ታሪካዊ ምዕራፍ ማስመዝገባቸውን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጽ ባስተላለፉት መልዕክት፤ “ታላቅ ወንድሜ እና ውድ ወዳጄ ክቡር ናሬንድራ ሞዲ፣ የዓለማችንን ትልቁን እና እጅግ ንቁ የሆነውን የዲሞክራሲ ማህበረሰብ ዘላቂ እምነት በማግኘት፣ ህንድን በራዕይ እና በቁርጠኝነት በተከታታይ ሶስት የዲሞክራሲያዊ የስልጣን ዘመናት በመምራት ላስመዘገቡት ታሪካዊ ስኬት የተሰማኝን ደስታ እገልጻለሁ” ብለዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ አመራር በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን ከድህነት ያወጣ መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ.ር)፤ የዲጂታል ሕዝባዊ መሰረተ ልማትን በከፍተኛ ደረጃ ያስፋፋ እና ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ የመሰረተ ልማት እድገትን በማምጣት ፈጣን የኢኮኖሚ መነቃቃትን ያስገኘ መሆኑንም ገልጸዋል።

በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በተከታታይነት ለደቡቡ የዓለም ክፍል (Global South) ጠንካራ ድምጽ በመሆን ማገልገላቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በመልዕክታቸው አስታውቀዋል።

#PMAbiyAhmed #Ethiopia #India #Diplomacy #Leadership #GlobalSouth #AMECO

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበአማራ ክልል የጎርፍ አደጋን ለመከላከል 157 ሚሊዮን ብር በጀት ተመድቧል።
Next articleሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እና ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን የ80 ሚሊየን ዶላር የብድር ስምምነት ተፈራረሙ።