
ባሕር ዳር: ሰኔ 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከአሜሪካ እና ኢራን ስምምነት ጋር በተያያዘ መግለጫ ሰጥተዋል
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ በቅርቡ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የተቀሰቀሰውን መጠነኛ ጥቃት እና ወታደራዊ ውጥረት ተከትሎ ከኢራን ጋር የሚደረገው ስምምነት “በመጨረሻው ምዕራፍ ላይ” እንደሚገኝ ነው የተናገሩት።
ፕሬዝዳንቱ እንደሚሉት ሁለቱ ሀገራት ውጥረቶችን ለማርገብ የሚያስችላቸው ስምምነት በቀጣዮቹ “ሁለት ወይም ሦሥት ቀናት ውስጥ” ሊፈረም እንደሚችል ፍንጭ ሰጥተዋል።
መግለጫው በሰሞነኛው የዓለም ዋንጫ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሁለቱ ሀገራት መካከል የሰነበተውን የፖለቲካ ትኩሳት እና ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት በእጅጉ ያረግበዋል ተብሎ ይጠበቃል።
#አሚኮ_ዜና #የውጭ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
