
ባሕር ዳር: ሰኔ 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በሕጻናት ላይ የሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደጉ ነው።
ምክኒያቶቹ ምንድን ናቸው?
በኢትዮጵያ 80 በመቶ ወላጆች ልጆቻቸው ኢንተርኔት ላይ ምን እንደሚሠሩ አንደማያውቁ ጥናቶች ማረጋገጣቸውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አሥተዳደር መረጃ ያሳያል።
ይህ ክፍተት ልጆችን ለሳይበር አዳኞች የተመቹ ያደርጋል።
ማኅበረሰቡ ተጎጂዎችን የመውቀስ (Victim-blaming) ዝንባሌ ልጆች ስቃያቸውን በውስጣቸው አፍነው እንዲቀሩ እና የደረሰባቸውን ጥቃት በግልጽ ወጥተው እንዳይናገሩ ያደርጋል።
ሰፊ የኢንተርኔት ተደራሽነት እና የታዳጊዎች ከፍተኛ ፍላጎት ያላንዳች የደህንነት ገደብ ሲገናኝ፣ ልጆች አደገኛ የኦንላይን ባህሪያትን (ለምሳሌ የግል መረጃን ማጋራት) እንዲላመዱ ያደርጋቸዋል።
#የዲጂታል ቁጥጥር (Parental Controls) ማድረግ
-በወላጆች ወይም በልጆች ስልክ ላይ የደህንነት ማስተካከያዎችን (እንደ Google Family Link, YouTube Kids) መጫን
-የማኅበራዊ ሚዲያ የግላዊነት ማስተካከያዎችን (Privacy Settings) በማስተካከል የልጆችን መረጃ “Private” ማድረግ
• አጥቂዎች እንዳይከታተሏቸው የስልካቸውን የቦታ መረጃ ማሳያ (Location services) ማጥፋት
#ግልጽ የውይይት ባሕልን ማሳደግ
-ኦንላይን ላይ የሚያስፈራ ነገር ካጋጠማቸው ሳይፈሩ እንዲናገሩ ግልጽነት የተሞላበት የቤተሰብ ድባብ መፍጠር።
#የሕፃናትን የዲጂታል ንቃት ማሳደግ
-ለማያውቁት ሰው የጓደኝነት ጥያቄ (Friend request) እንዳይቀበሉ ማስገንዘብ
• የይለፍ ቃል (Password)፣ ፎቶ፣ እና የግል መረጃን ለማንም እንዳያጋሩ ማሳሰብ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
