በኮምቦልቻ ከተማ 145 ኢንዱስትሪዎች የሚሳተፉበት የኢትዮጵያ ታምርት ክልላዊ የማጠቃለያ መድረክ ዛሬ ይካሄዳል።

10

 

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 30/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በዚህ መድረክ ላይ ለመታደም ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል እና ሌሎችም ከፍተኛ መሪዎች ተገኝተዋል። ክልላዊ የንቅናቄ ማጠቃለያ መርሐ ግብሩ “ኢትዮጵያ ታምርት ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት” በሚል መሪ መልዕክት ነው የሚካሄደው።

በክልሉ ውስጥ የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች ምርቶቻቸውን አቅርበው የሚያስተዋውቁበት እና የሚሸጡበት ኤክስፖም ተዘጋጅቷል።

ንቅናቄው አምራቾች ምርታቸውን እንዲያስተዋውቁ፤ የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩ እና ችግሮቻቸውን ተቀርፈውላቸው የተሻለ እንዲያመርቱ የሚያስችል ነው።

በኤክስፖው 145 ኢንዱስትሪዎች እንደሚሳተፉ ተገልጿል።

ርእሰ መሥተዳድሩ በቆይታቸው “ኢትዮጵያ ታምርት” ክልላዊ የማጠቃለያ መርሐ ግብር ኤክስፖን ይከፍታሉ፤ ከባለሀብቶች እና ከባለድርሻ አካላት ጋርም ይወያያሉ።

ዘጋቢ፦ ታርቆ ክንዴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article🌾በአማራ ክልል በመኸር እርሻ ለመሸፈን ከታቀደው መሬት ውስጥ 3 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሄክታሩ በኩታገጠም እርሻ የሚለማ ነው።
Next article🏙 ኮሪደር ልማት ከከተማ ውበት በላይ የሥራ ባሕልን በእጅጉ እየቀየረ ነው ።