ከሰሞኑ ጣና ሃይቅ አካባቢ ምን ተከሰተ?

20

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያዎች ጣና ሃይቅ ውስጥ በሚገኙ ገዳማት ፍንዳታ ተከሰተ፤ በገዳማት ላይ ቃጠሎ ተከሰቷል የሚሉ መረጃዎች እየተዘዋወሩ ነው።

ጣና ሃይቅ አካባቢ የተፈጠረው ምንድን ነው? ከአሚኮ እውነታ ማጣሪያ!

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መመሪያ አዛዥ ኮማንደር ዋለልኝ ቢምረው በጣና ሃይቅ በተለምዶ አባ ገሪማ በሚባለው አካባቢ የእሳት ቃጠሎ ረቡዕ ሌሊት መከሰቱን ገልጸዋል።

ሀሙስ ማለትም27/09/18 ዓ.ም ወደ ቦታው ማምረታቸውን እና በቦታው የእሳት ቃጠሎ መኖሩን ስለማረጋገጣቸው አንስተዋል።

👉የቃጠሎው ምክኒያት?

በአካባቢው ጨፌ/ሳር/ አጭደው በመሸጥ የሚተዳደሪ ግለሰቦች የተሻለ ሳር እንዲበቅል በማሰብ እንዳቃጠሉት ይገመታል አሉን ኮማንደር ዋለልኝ። እርግጠኛ ኾኖ መናገር ግን እንደማይቻል ነው የተናገሩት።

ነገር ግን አካባቢው አርጥብ እና ረገረጋማ በመኾኑ ቃጠሎው ኾን ተብሎ የተደረገ ስለመኾኑ እርግጠኛ መኾን ይቻላል ብለዋል?

✍️አኹንስ በምን ኹኔታ ላይ ነው?

አካባባው ረገረጋማ በመኾኑ ረቡዕ ሌሊት የተከሰተውን ቃጠሎ አኹንም መሉ በሙሉ ማስቆም እንዳልተቻለ ኮማንደሩ ገልጸዋል። እሳቱን በሰው ሃይል ለማጥፍት እየተሠራ ነው ብለዋል።

👉ሲጠቃለል

እሳት እና ጭስ ቢታይም ፍንዳታ እንደተከሰተ እና ገዳማት እንደተቃጠሉ የሚዘዋወረው መረጃ እውነት አይደለም።

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleጽንፈኝነት በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም።
Next article“ምርጫውን ለማደናቀፍ የውጭ ባዳዎች እና የውስጥ ባንዳዎች ያደረጉት ዕቅድ ከሽፏል” የሰላም ሚኒስትር ሙሐመድ እድሪስ