
ባሕር ዳር: ግንቦት 26/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ትናንት በመጭው ክረምት ማለትም ከሰኔ እስከ መስከረም ባሉት ወራት በምሥራቅ አፍሪካ ከሚጠበቀው በታች የዝናብ ኹኔታ እንደሚኖር የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ኢጋድ የአየር ንብረት ትንበያ እና መተግበሪያ ማዕከል በቅርቡ መግለጹ ይታወቃል።
በምክኒያት የተነሳው ደግሞ የኢልኒኖ ተጽዕኖ ነው።
በኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዮት የምዕራብ አማራ ሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል የሚቲዮሮሎጂ ሳይንስ ረዳት ተመራማሪ እንደግ አንለይ
ከክልሉ ከዓመታዊ የዝናብ መጠን ውስጥ ከ65 እስከ 90 በመቶ የሚኾነው ድርሻ በክረምት ወቅት የሚሸፈን በመኾኑ ለክልሉ ግብርና እና ኢኮኖሚ ወሳኝ ጊዜ ነው ብለዋል።
ይኹን እንጂ የዘንድሮው የክረምት ወቅት በአብዛኛው ከቀላል እስከ መካከለኛ በኾነ የኢልኒኖ ተጽዕኖ ሥር እንደሚቆይ ነው ባለሙያው የገለጹት።
ይህም በዝናብ ሥርጭቱ እና መጠኑ ላይ የራሱ የኾነ አሉታዊ ጫና ይኖረዋል ብለዋል።
#ነገር ግን በአማራ ክልል አብዛኛዎቹ አካባቢዎች የሚኖረው የዝናብ መጠን ከመደበኛ ጋር የተቀራረበ እንደሚኾን ይጠበቃል ነው ያሉት።
በእነዚህ አካባቢዎች ዝናቡ ከመደበኛው መጠን በታች የመኾን እድሉም ከፍተኛ መኾኑን በመረዳት በተለይ አርሶ አደሮች አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል።
ይህ ኹኔታ የሰብል እርጥበት እጥረት ሊያስከትል ስለሚችል አርሶ አደሮች የሚገኘውን እርጥበት በአግባቡ የመያዝ እና የማቆር ሥራዎችን በልዩ ትኩረት ሊያከናውኑ ይገባል ብለዋል።
በአጭር ጊዜ የሚደርሱ የሰብል ዝርያዎችንም መዝራት እንደሚገባ መክረዋል።
ስለዚህ ለጎርፍ ተጋላጭ የኾኑ አካባቢዎችን በመለየት የመከላከያ ሥራዎችን ማከናወን ይገባል ብለዋል።
#ከኢንስቲትዩቱ የሚወጡ አዳዲስ መረጃዎችን እና ማሻሻያዎችን በንቃት በመከታተል አስፈላጊ የጥንቃቄ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባም መክረዋል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
