
ደሴ፡ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የክልል ምክር ቤት እጩ ከድር ይመር በደሴ ከተማ በተወከሉበት የምርጫ ክልል ድምጽ ሰጥተዋል።
እስካሁን ያለው የምርጫ ሂደት ፍፁም ሰላማዊ ነውም ብለዋል። ኅብረተሰቡ ይበጀናል ያለውን በካርዱ እየመረጠ ይገኛልም ነው ያሉት አቶ ከድር።
እስከአሁን የምርጫ ሂደቱ መልካም መኾኑን ያነሱት እጩ ተወዳዳሪው ምርጫ የስልጣኔ መገለጫ በመኾኑ ሁሉም ዜጋ ካርዱን በአግባቡ አንዲጠቀም ጠይቀዋል።
ዘጋቢ:- ተመስገን አሰፋ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
