
ባሕር ዳር: ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በባሕር ዳር ምርጫ ክልል ጣና 02 ምርጫ ጣቢያ ሲመርጡ ያገኘናቸው የ90 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋዋ ምንትዋብ አዘነልኝ መብታቸውን መጠቀማቸውን ገልጸዋል።
ከዚህ በፊት በተካሄዱ ስድስት ምርጫዎች ላይ ተሳታፊ እንደነበሩም አስታውሰዋል። ዛሬም ሀገርን ያሥተዳድራል፤ ሕዝቡን ይመራል ላልኩት ፓርቲ ድምጽ ሰጥቻለሁ ብለዋል።
ወይዘሮ ምንትዋብን ደግፈው አብረው ያገኘናቸው ልጃቸው የሠራሽ አድማሱ ከእናቴ ጋር ሀገሬን ያገለግላል የምለውን መሪ ለመምረጥ መጥቻለሁ ብለውናል።
ካርድ አውጥቶ መቅረት ኀላፊነትን መሸሽ እንደኾነም አንስተዋል።
ዘጋቢ፦ ሮዛ የሻነህ
የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ !
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
