
ባሕር ዳር: ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ማድረግ እንደማይቻል ብዙዎች የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ሠርተዋል ብለዋል። ይሁን እንጅ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደተለመደው በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከፍተኛ የጀግንነት መንፈሱን እያሳየ ነው ብለዋል።
ሕዝቡ ከጥዋት ጀምሮ ድምጹን እየሠጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሀገረ መንግሥትን እና የዴሞክራሲ ሥርዓትን ለመገንባት እየታተር ይገኛል፤ ለዚህም የማንንም ግፊት ሳይሻ መሪውን በነጻነት እየመረጠ ይገኛል ነው ያሉት።
ሕዝቡ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች እና የሚዲያ ተቋማት በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እያደረጉት ላለው ተጋድሎም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስጋና አቅርበዋል።
በምርጫው ያሸነፉት በታማኝነት ሕዝብን እንዲያገለግሉ፤ የተሸነፉት ደግም ውጤቱን በጸጋ መቀበል ይገባል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመጣውን ውጤት በጸጋ ለመቀበልም ዝግጁ ነን ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በትውልድ ቀያቸው በበሻሻ ድምፅ ሰጥተዋል።
ዘጋቢ፦ ቴዎድሮስ ደሴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
