
ባሕር ዳር: ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ልዑክ መሪና የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላማዊ ሁኔታ መጀመሩን ገልጸዋል።
ድምፅ መስጠት ዜጎች የሚወክሏቸውን መሪዎች በነፃነት የሚመርጡበት ትልቅ ዴሞክራሲያዊ መብታቸው ነው ብለዋል።
በምርጫ ጣቢያዎች የተመለከቱት ነገር መልካም እንደነበር የጠቀሱት ኬንያታ፤ ይህ በሰላምና በሥርዓት የመምረጥ ሂደት ቀኑን ሙሉ እንዲቀጥል ተመኝተዋል።
“ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋና ከተማ ናት፤ በዚህች ሀገር የሚመዘገብ ስኬት ለመላው አህጉር ብርሃን ነው” በማለት ለኢትዮጵያ ሕዝብ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
በቴዎድሮስ ደሴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
