
ደብረማርቆስ፡ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪዎች 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ እያካሄዱ ይገኛሉ።
በከተማዋ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች መራጮች ድምፃቸውን እየሰጡ ነው።
አሚኮ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ነፃ ኾነው ለሚፈልጉት ድምፃቸውን ስለመስጠታቸው ተናግረዋል።
ምርጫ የአንድን ሀገር መፃኢ ዕድል የሚወስን ቁልፍ ጉዳይ መኾኑንም ገልጸዋል።
ሀገርን ለማስቀጠል እንዲሁም ሰላም እና ዕድገትን ለማረጋገጥ ምርጫ ቁልፍ ሚና ይጫወታል ነው ያሉት።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
