
ደብረ ታቦር: ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ታቦር ከተማ ልጅ ያዘሉ እናቶች፣ አካል ጉዳተኞች እና ነዋሪዎች ድምጽ እየሰጡ ነው።
አቶ በለጠ ሞሳ አካል ጉዳተኛ ናቸው። አካል ጉዳተኛ መኾናቸው ግን በጠዋት ተነስተው ድምጽ ከመስጠት አላገዳቸውም።
ያለማንም ጣልቃ ገብነት ዴሞክራሲያዊ በኾነ መንገድ የሚጠቅማቸውን እንደመረጡ ነግረውናል።
ሀገር ሰላም እንዲኾን እና ሠርተን እንድንበላ ፍላጎቴ ስለኾነ በጠዋት ተነስቼ ለመምረጥ አነሳስቶኛል ብለውናል።
ሌላኛዋ ነዋሪ አዳነች እጅጉ ደግሞ ልጇን አዝላ በጠዋት ድምጽ ከሰጡት መካከል ናቸው።
ለሀገር ሰላም ያላቸው ምኞት በጠዋት ተነስተው እንዲመርጡ እንዳነሳሳቸው አጫውተውናል።
#Ethiopian electio #ኢትዮጵያ ትመርጣለች
ዘጋቢ፦ አድኖ ማርቆስ
የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ !
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
