
ፍኖተ ሰላም፡ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በፍኖተ ሰላም ከተማ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዜጎች ድምጽ እየሰጡ ነው።
አቅመ ደካሞች፣ አካል ጉዳተኞ እና ሌሎችም የኅብረተሰብ ክፍሎች በቀጠሯቸው ተገኝተው ድምጻቸውን ሰጥተዋል።
ጸጋዬ አይናለም የከተማዋ ነዋሪ ናቸው። አካል ጉዳተኛነታቸው ሳይገድባቸው ከአሁን በፊት በነበሩ ምርጫዎች መሳተፋቸውን ነግረውናል።
በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫም ቀዳሚ ኾነው ከተገኙት መካከል ናቸው። ብዙ መቆምም ኾነ መቀመጥ አልችልም፤ ግን ደግሞ መምረጥ ነበረብኝ፤ ለዚያም ፀሐይ ሳይበረታ በጠዋቱ ይበጀኛል የምለውን መርጫለሁ ነው ያሉት።
በመረጡት ለመተዳደር የምርጫ ካርድን በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባም መልዕክት አስተላልፈዋል።
ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!
ዘጋቢ፦ ስማቸው አጥናፍ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
