“ቀድመን በጠዋት የተሰለፍነው ሀገራዊ ኀላፊነታችን ለመወጣት ነው” የሰቆጣ ከተማ ነዋሪዎች

3

 

ሰቆጣ: ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ሰቆጣ ምርጫ ክልል 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ መካሄድ ጀምሯል።

በሰቆጣ ምርጫ ክልል ጣቢያ 9 የሚገኙ የሰቆጣ ከተማ ነዋሪዎችም ምርጫውን በጉጉት ይጠብቁት እንደነበረ ገልጸዋል።

አቶ አያሌው ጣፈጠ እና ወይዘሮ ደርባ ተበጀ የሰቆጣ ከተማ ነዋሪ ናቸው። ሌሊት 11 ሰዓት ጀምረው ለመምረጥ እንደወጡ ገልጸዋል።

“ቀድመን በጠዋት የተሰለፍነው ለወረፋ ሳይኾን ሀገራዊ ኀላፊነታችን ለመወጣት ነው” ብለዋል።

ዘጋቢ፦ደጀን ታምሩ

የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ !

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleበባሕር ዳር ከተማ መራጮች ድምጽ መስጠት ጀምረዋል።
Next article🇪🇹🗳️ በደብረ ማርቆስ ከተማ መራጮች ድምጽ እየሰጡ ነው።