
ባሕር ዳር: ግንቦት 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሊካሄድ ቀናት ብቻ ቀርተውታል።
በዚህ ምርጫ የመንግሥት ሠራተኞችም የዜግነት ግዴታቸውን እና መብታቸውን ለመጠቀም ካርድ ወስደው የምርጫውን ቀን እየተጠባበቁ ይገኛሉ።
በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር የጃዊ ወረዳ እና የፈንድቃ ከተማ አሥተዳደር የሚሠሩ የመንግሥት ሠራተኞች ጣሰው አዲስ እና ፈንታነሽ መኮነን የምርጫው ዕለት ለመምረጥ የሚያስችላቸውን ካርድ ወስደው ቀኑን እየተጠባበቁ እንደሚገኙ ለአሚኮ ተናግረዋል።
የነገይቱን ኢትዮጵያ እና ሕዝቡን ሊጠቅም የሚችል ፓርቲን ለመምረጥ ዕድል የሚሰጠውን ካርድ በማውጣታችን ደስተኛ ነን ብለዋል።
ምርጫው ስኬታማ እንዲኾን የመንግሥት ሠራተኞች የበኩላቸውን እየተወጡ እንደኾነም ጠቅሰዋል።
“በወሰድነው ካርድ የሚኾነንን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል” ነው ያሉት።
ዘጋቢ፦ሰለሞን ስንታየሁ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
