ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በያቤሎ ከተማ የተገነባውን የቦረና ባሕል ማዕከል መርቀው ሥራ አሥጀመሩ።

4

 

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በ2013 ዓ.ም የመሰረት ድንጋይ ተቀምጦለት የነበረውና ዛሬ ለአገልግሎት ክፍት የሆነው የባህል ማዕከል፤ በመደመር መጽሐፍ ሽያጭ የተገነባ ሲሆን በ57 ነጥብ 6 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ መኾኑ ተገልጿል።

ማዕከሉ የገዳን ሥርዓት ለማሳየት በልዩ ሁኔታ ዲዛይን የተደረገ ሲሆን በአንድ ጊዜ እስከ 2 ሽህ ሰዎች የማስተናገድ አቅም ያለው የስብሰባ አዳራሽ እና የቅርስ ሙዚየምን አካቶ የተገነባ ነው። ማዕከሉ የቦረናን ሕዝብ ባሕል፣ ታሪክ እና ፍልስፍና ለትውልድ የማሸጋገር ቁልፍ ሚና እንደሚኖረው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት ገልጸዋል።

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleበፍኖተ ሰላም ከተማ የተጀመረው የኮሪደር ልማት የከተማዋን ገጽታ እየቀየረ ነው።