የኢድ አል-አደሃ (አረፋ) በዓል በባሕር ዳር ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው።

3

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 1 ሺህ 447ኛው የኢድ አል-አደሃ (አረፋ) በዓል በባሕር ዳር ከተማ የሃይማኖቱ አባቶች፣ ተከታዮች እና ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

የባሕር ዳር ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ዋና ሰብሳቢ ሼህ ሙሐመድ ሳይድ 1 ሺህ 447ኛው የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓል የመረዳዳት፣ የደግነት፣ የመተሳሰብ እና የተቸገሩትን የመጎብኘት እሴት የሚጎለብትበት እንዲኾን ተመኝተዋል።

የሃይማኖቱ ተከታዮች በዓሉን ሲያከብሩ የተቸገሩ ወገኖችን በማሰብ እና የአብሮነት ባሕልን በማጠናከር መሆን እንዳለበትም አሳስበዋል።

የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ለሙስሊሙ ማኅበረሰብ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዓሉ የከተማዋን ሰላም እና ልማት ይበልጥ ለማጠናከር እና የእርስ በርስ ትስስርን ለማጎልበት መልካም አጋጣሚ መኾኑን ነው የተናገሩት።

ሕዝበ ሙስሊሙ እያደረገ ያለውን የሰላም እና የልማት ተግባር አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባልም ብለዋል።

#ኢድ አል አደሃ #አረፋ #ባሕር ዳር #አሚኮ #ኢትዮጵያ🇪🇹

ዘጋቢ፦ ቴዎድሮስ ደሴ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleወደ ፈጣሪ የሚቀራረቡባቸው የላቁት የዙልሂጃ ቀናት
Next article🕋 “የፅድቋ ከተማ መካ”