“ከግንቦት 20/2018 ዓ.ም ጀምሮ የጥሞና ጊዜ ነው” ምርጫ ቦርድ

13
አዲስ አበባ፡ ግንቦት 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በመጪው ሰኞ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ይካሄዳል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቅድመ-ምርጫ ሥራዎች እና የድምፅ መስጫ ቀንን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።
የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላተወርቅ ኃይሉ ለጠቅላላ ምርጫው የሚያስፈልገው የቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ መጠናቀቁን ገልጸዋል።
ከየካቲት 18/2018 ዓ.ም ጀምሮ በተከናወነው የመራጮች ምዝገባ ከ50 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ዜጎች ተመዝግበዋል።
በዚህ የምዝገባ ወቅት የተከሰቱ እና ጥያቄን የሚያጭሩ ሁነቶች በተከሰቱባቸው አካባቢዎች የመራጮች ምዝገባዎች እንዲሰረዙ እና ድምጽ በሚሰጥበት ቀን ምዝገባው እንዲከናወን ተወስኗል።
ኢጋድ እና የአፍሪካ ኅብረት ምርጫውን ለመታዘብ ታዛቢዎችን ይልካሉ ተብሎ ይጠበቃል ነው ያሉት።
ከሚዲያ ተቋማት ጋር በተገናኘ ይሄንን ጠቅላላ ምርጫ ለማከናወን በሚደረገው ሂደት 64 የሚዲያ ተቋማት እውቅና ተሰጥቷቸው ሥራዎች እየሠሩ ይገኛሉ ብለዋል።
ከግንቦት 20/2018 ዓ.ም ጀምሮ የጥሞና ጊዜ ሲኾን ምንም አይነት የቅስቀሳ ተግባር እንደማይከናወን ሰብሳቢዋ አስታውቀዋል። በቀሩት ቀናት ብቻ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምረጡኝ ቅስቀሳቸውን እንዲያከናውኑ አሳስበዋል።
ከምርጫ ሂደቱ ጋር በተገናኘ ማንኛውም ሰው ጥቆማ ካለው በ6214 አጭር የስልክ መስመር ጥቆማ ማድረስ ይችላል ተብሏል።
ዘጋቢ- ሐናማርያም መስፍን
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
Previous articleእንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል አድሐ በዓል አደረሰን፣ አደረሳችሁ!
Next articleየብልጽግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ በሰላም መጠናቀቁን የአማራ ክልል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ።