
ባሕር ዳር: ግንቦት 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተገልጋዮችን ወጭ፣ ጊዜ እና እንግልት የሚቀንሱ ዘመናዊ የዳኝነት አገልግሎት መስጫ መሠረተ ልማቶችን በመገንባት ላይ ይገኛል።
ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ እየዘረጋቸው ካሉ ዘመናዊ አሠራሮች መካከል ባለጉዳዮች ፍርድ ቤት በአካል መሄድ ሳይጠበቅባቸው ባሉበት ኾነው አገልግሎት የሚያገኙበት የጥሪ ማዕከል ተጠቃሽ ነው።
ይህም 6152 የጥሪ ማዕከል ሲኾን ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች ውስጥ
ተገልጋዮች ከግንቦት 17/2018 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ወደ 6152 የጥሪ ማዕከል በመደወል የፈለጉትን መረጃ ባሉበት ኾነው ማግኘት እንደሚችሉም ከክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
