ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ራሳቸውን እንዲያስተዋውቁ የአሚኮ ፍትሐዊነት ምን ድረስ ነበር?

2
ባሕር ዳር: ግንቦት 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሊካሄድ ቀናት ቀርተውታል። አሚኮም የመራጮችን ግንዛቤ የሚያሳድጉ ዘገባዎችን እና ተፎካካሪ ፓርቲዎችም ይዘውት የቀረቡትን ሃሳብ ለሕዝብ እንዲያደርሱ ሥራዎችን እየሠራ ነው።
#ለመኾኑ ተፎካካሪ የፖለቲካዎች በእስካኹን የምርጫ ዝግጅታቸው አሚኮ በፍትሐዊነት አገዛቸው ወይስ?
የብልጽግና ፓርቲን ወክለው ሃሳብ የሰጡት መስፍን አበጀ(ዶ.ር) በኢትዮጵያ እየተገነባ ያለውን አዲስ የፖለቲካ ባሕል ለማጎልበት እና በሃሳብ ብልጫ አሸናፊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሕዝብን እና ሀገርን እንዲመሩ ለማድረግ መረጃን ወደ ሕዝብ ተደራሽ በማድረግ አሚኮ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደነበረው ተናግረዋል።
ብልጽግና ፓርቲ የፖሊሲ ሃሳቦችን እና መልዕክቶቹን በአግባቡ ለሕዝብ እንዲያደርስ አሚኮ እንዳገዘው ተናግረዋል።
👉ይበልጣል አድማሴ ደግሞ ኢዜማ ፓርቲን ወክለው ሃሳብ የሰጡን ናቸው። ፓርቲያቸውን ወክለው የተለያዩ ክርክሮችን በአሚኮ አማካኝነት ማድረጋቸውን ተናግረዋል።
ከዚህ በፊት ባልተሄደበት መንገድ ሚዲያው ደግፎናል ለዚህም ምሥጋና ይገባዋል ብለዋል። የአራተኛ መንግሥት ሚናውን በአግባቡ መወጣቱንም መስክረዋል።
👉የአዴኃን የፖለቲካ ፓርቲን የወከሉት ይኼነው መስፍንስ ምን አሉ?
አዴኃን በክርክሮች እና የዘገባ ሽፋኖች ላይ አሚኮ ለነበረው አስተዋጽኦ ዕውቅና ሰጥተናል አሉን። ብዙም ባልተለመደ ኹኔታ አሚኮ የፓርቲው ሀሳቦች እና መልዕክቶችን ለማኅበረሰቡ በአግባቡ አንዲደርስ ትልቅ እገዛ ማድረጉንም አንስተዋል።
👉አሚኮ ምርጫን ዋና የዘገባ አካል አድርጎ በርካታ ዘገባዎችን ሲሠራ መቆየቱን የገለጹት ደግሞ የአብኑ መልካሙ ጸጋየ ናቸው። ከሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች መረጃ በመውሰድ እና ለሕዝብ በማሠራጨት በፍሐዊነት ሚዲያው ሚናውን በአግባቡ መወጣቱንም መስክረዋል።
የፖሊሲ አማራጮች እና ሃሳቦች በክርክር ለሕዝብ እንዲደርሱ አሚኮ ወሳኝ ሚና መጫወቱንም አቶ መልካሙ ተናግረዋል።
ዘጋቢ፦ ሮዛ የሻነህ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
Previous article“ያቀድነውን እንደምንሠራ የፈጸምናቸውን ኘሮጀክቶች በተግባር አሳይተን ቀርበናል” አቶ ፍስሀ ደሳለኝ
Next articleየአማራ ክልል የፍርድ ቤቶች ጥሪ ማዕከል በሙሉ አቅሙ ሥራ ጀመረ።