ወልድያ: ግንቦት 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ወሎ ዞን መርሳ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ እና የምርጫ ቅስቀሳ ማጠቃለያ ተካሄዷል።
መርሳ ከተማ ከንቲባ ሙሐመድ ያሲን ከተማዋን ለኑሮ እና ለሥራ ምቹ ለማድረግ የኮሪደር ልማት እየተሠራ መኾኑን ገልጸዋል።
ከኢንቨስትመንት አኳያም ዘመናዊ ሆቴል እና የገበያ ማዕከል ግምባታ እየተሠራ ነው ያሉት ከንቲባው ለተጨማሪ የልማት ሥራ ከ60 ሄክታር በላይ መሬት ተዘጋጅቶ አልሚ ባለሀብቶችን እየተጠባበቀ ነው ብለዋል።
የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አራጌ ይመር ፓርቲው ሁለንተናዊ ብልጽግናዋ የተረጋገጠ ሀገር እየገነባ መኾኑን አስረድተዋል። ብልጽግና በእሳት እየተፈተነ የመጣ ፓርቲ ነው ያሉት አቶ አራጌ ይመር በሁሉም መስክ ሀገር እየገነባ ሕዝብ እንዲጠቀም ያደረገ የሀገር ባለውለታ ነው ብለዋል።
አንደ ምርጫ ክልላችንም ግጭትን አስወግደን በየአካባቢያችን ያሉ ፀጋዎችን በመለየት የሀብሩ መርሳ ሕዝብን ተጠቃሚ እናደርጋለን ሲሉም ቃል ገብተዋል።
የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ ፍስሀ ደሳለኝ ከተሞችን ለነዋሪው ምቹ አድርገን፣ የኀይል አቅርቦት እና የቱሪዝም መዳረሻን አስፍተን የሀገር ሉዓላዊነትን አስከብረን፣ የታፈረች ሀገር ግምባታን አያሳለጥን ነው ብለዋል።
“ያቀድነውን እንደምንሠራ የፈጸምናቸውን ኘሮጀክቶች በተግባር አሳይተን ቀርበናል” ያሉት አቶ ፍስሃ ሕዝቡም ከብልጽግና ፓርቲ ጎን እንዲኾን ጠይቀዋል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
