
ደሴ: ግንቦት 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ብልጽግና ፓርቲ በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የአደባባይ የምርጫ ቅስቀሳ እና የዕጩዎች ትውውቅ መርሐግብር አካሂዷል።
በደላንታ ዳውንት ምርጫ ክልል የፓርቲ እጩዎች ከሕዝቡ ጋር ትውውቅ አድርገዋል።
በርካታ ቁጥር ያላቸው የፓርቲው ደጋፊዎችም አደባባይ በመውጣት ለፓርቲው ያላቸውን ድጋፍ አሳይተዋል። ሰላም እንዲሰፍን እንፈልጋለን ያሉት የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች ምርጫው ነጻ እና ተዓማኒ ኾኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እንደሚወጡም ገልጸዋል።
በድምጽ መስጫው ዕለትም ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ሰላምን ያረጋግጣል፣ ሀገርን ያሻግራል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
በብልጽግና ፓርቲ የደላንታ ወረዳን በሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ለመወከል የሚወዳደሩት የደላንታ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ አያሌው በሪሁን፤ ምርጫ የሕዝብ አደራ መቀበያ በመኾኑ በኅብረተሰቡ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ስለመኾናቸው አስረድተዋል።
በብልጽግና ፓርቲ በደላንታ ዳውንት ምርጫ ክልል የክልል ምክር ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ እና በፓርቲው የደቡብ ወሎ ዞን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተስፋ ዳኛው ፓርቲው ኢትዮጵያ የሚገጥሟትን የህልውና ፈተናዎች በመሻገር፣ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማሳካት የሚያስችል አቅም ያላት ሀገር እንድትኾን እየሠራ መኾኑን ገልጸዋል።
በደላንታ ዳውንት ምርጫ ክልል የክልል ምክር ቤት ዕጩ እና የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ አማካሪ ኤርሚያስ መኮንን (ዶ.ር)
የሀገር ዕድገት እና ብልጽግና ያለ ሰላም ስለማይታሰብ የተጀመሩ መሠረተ ልማቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ኅብረተሰቡ ለሰላሙ ዕውን መኾን አስፈላጊውን ሁሉ እንዲያደርግ እና ከመንግሥት ጎን እንዲቆምም ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ፦ አንተነህ ፀጋዬ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
