“ብልጽግና ፓርቲ ቃልን በተግባር ያረጋገጠ ሀገራዊ ፓርቲ ነው” አቶ እንድሪስ አብዱ

6
ከሚሴ: ግንቦት 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ”ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ መልዕክት የብልጽግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ እና የምረጡኝ ቅስቀሳ በከሚሴ ከተማ ተካሂዷል።
በድጋፍ ሰልፉ የከሚሴ ከተማ እና የደዋ ጨፋ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ አባላት እና ደጋፊዎች ተሳትፈዋል።
የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኀላፊ እንድሪስ አብዱ “ብልጽግና ፓርቲ ቃልን በተግባር ያረጋገጠ ሀገራዊ ፓርቲ ነው” ብለዋል።
የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አሥተዳዳሪ አሕመድ አሊ ብልጽግና ፓርቲ ከዚህ በፊት ያልተፈጸሙ የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ሥራዎችን በገጠር እና በከተማ የተገበረ ፓርቲ ነው ብለዋል።
የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ እና ፍትሐዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።
ዘጋቢ:- ይማም ኢብራሒም
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
Previous articleምርጫ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም አማራጭ የሌለው ሕገ መንግሥታዊ ግዴታ ነው።
Next articleየሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔዎችን አሳለፈ።