“ብልጽግና ፓርቲ ደብረታቦር ከተማን ወደ ሚመጥናት ከፍታ ለማድረስ ይሠራል” አቶ ሲሳይ ዳምጤ

2
ደብረታቦር: ግንቦት 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረታቦር ከተማ “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ መልዕክት የብልጽግና ፓርቲ ደጋፊዎች የድጋፍ ሰልፍ እና የምርጫ ቅስቀሳ አካሂደዋል።
የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ኀይለኢየሱስ ሰለሞን የረጅም ጊዜ የሕዝብ ጠያቄ የነበረው የኀይል የሰብስቴሽን ችግር መፈታቱን ጠቅሰው ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት፤ የደብረ ታቦር ቲቺንግ ሪፈራል ሆስፒታል እና ሌሎች የልማት ሥራዎች እየተገነቡ መኾናቸውን ተናግረዋል። ልማቶቹም ደብረታቦር ከተማ እና አካባቢው የብልጽግና ፓርቲ የልማት ሥራዎች ተቋዳሽ መኾኑን ማሳያ እንደኾኑ ጠቁመዋል።
ብልጽግና ወጣቶች ሀገር ተረካቢ ብቻ ሳይኾኑ የዛሬ የሀገር ግንባታ ዋና መሪ መኾናቸውን፤ እናቶች የሰላም እና የአንድነት ምልክቶች፤ ምሁራን ደግሞ በሀገር ግንባታ ሂደት የማይተካ ሚና የሚወጡ መኾናቸውን ያምናል ነው ያሉት።
በሰልፉ የተገኙት የአማራ ክልል መሬት ቢሮ ኀላፊ ሲሳይ ዳምጤ “በደብረ ታቦር ከተማ እየታየ ያለው የልማት እንቅስቃሴ የብልጽግና ፓርቲ የለውጥ እና የብልጽግና ጉዞ ተጨባጭ ማሳያ ነው” ብለዋል።
የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን በማጠናከር ታሪካዊቷ ደብረ ታቦር ከተማን ወደሚገባት ከፍታ ለማድረስ እንደሚሠራም አረጋግጠዋል።
የደብረታቦር እና አካባቢው ማኅበረሰብ በነቂስ ወጥቶ ለሰላም እና ለልማት ያለውን ጽኑ አቋም አሳይቷልም ብለዋል።
ሕዝቡ ባወጣው ካርድ እንዲመርጥ እና የተጀመረውን የሀገረ መንግሥት ግንባታ እና የለውጥ ሥራ እንዲያስቀጥል አቶ ሲሳይ ዳምጤ ጥሪ አቅርበዋል።
የሰልፉ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በከተማዋ የተጀመሩ የልማት ሥራዎች የሚያበረታቱ መኾናቸውን ተናግረዋል።
ምርጫው ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅም የተጀመሩ የሰላም ሥራዎችን እንደሚያስቀጥሉም አረጋግጠዋል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
Previous articleምርጫው ሰላማዊ እና ፍትሐዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ ሁሉም ኀላፊነቱን ሊወጣ ይገባል።
Next article“ጎንደር የኢትዮጵያ አንድነት እና የሉዓላዊነት አርማ ኾና ዘልቃለች” አማኑኤል ፈረደ (ዶ.ር)